የፊፋ ፕሬዚደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የቴሌቪዥን አሰራጮች የሴቶች ዓለም ዋንጫን ከወንዶች ለ"100 ጊዜያት ባነሰ" ለማሰራጨት በማሰባቸው ትችት ሰነዘሩ።
ኢንፋኒቶ ቅሬታቸውን ከኦክላንድ ያሰሙት ቅዳሜ ዕለት በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ የሚዘጋጀው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ምደባ ዕጣ ከመውጣቱ ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብለው ነው።

Draw Assistant Maia Jackman draws England during the FIFA Women's World Cup 2023 Final Draw at the Aotea Centre on October 22, 2022 in Auckland, New Zealand. Credit: Harold Cunningham - FIFA/FIFA via Getty Images
የማናቸውንም የቴሌቪዥን ኩባንያዎች ስም ሳይጠቅሱ "አሰራጮች ከወንዶች የዓለም ዋንጫ በ100 ጊዜያት ባነሰ" የስርጭት ሰዓታት ለማስተላለፍ እንደሚሹ ዕቅዶቻቸውን እንዳስታወቋቸው በቅሬታ አመልክተዋል።
አያይዘውም ፊፋ ባለፉት ቅርብ ዓመታት ለሴቶች እግር ኳስ አንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ ማድረጉን ገልጠዋል።
በ2015 እና 2019 የሴቶች ዓለም ዋንጫ የፋይናንስ ኪሳራ ያስከተለ ቢሆንም፤ ፊፋ ለመጪው የዓለም ዋንጫ 400 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ መድቧል።
ለመጀመሪያ ጊዜ 32 ቡድናት ከጁላይ እስከ ኦገስት የሚሳተፉበት የዓለም ዋንጫ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከፍተኛ ፍላጎትን ያሳድራል ተብሎ ይጠበቃል።