በኦሪጎን22 የዓለም አትሌቲክስ 5000 ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ 14 ደቂቃ 46.29 ሰከንዶች በመጨረስ የዓለም ሻምፒዮን ድል አድራጊ ሆና የወርቅ ሜዳል ተሸላሚ ሆናለች።
ጉዳፍን ተከተለው ኬንያዊቷ ቢትሪስ ቼቤት 14 ደቂቃ 46.75 ኢትዮጵያዊቷ ዳዊት ስዩም 14 ደቂቃ 47.36 ሰከንዶች በመጨረስ የብርና ነሐስ ሜዳል ባለቤቶች ለመሆን በቅተዋል።
የኦርጎን22 የ5ሺ ሜትር የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዋ ጉዳፍ ውድድሯን በአሸናፊት ከጨረሰች በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠችው ቃለ ምልልስ "በውጤቱ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ይህ ድል ለመላው ኢትዮጵያ ነው" ብላለች።

Silver medalist Beatrice Chebet of Team Kenya, gold medalist Gudaf Tsegay of Team Ethiopia, and bronze medalist Dawit Seyaum of Team Ethiopia. Source: Getty
የኦሪጎን22 የ10000 ሜትር የወርቅ ሜዳል ባለቤትና የ5000 ሜትር ባለ ክብረወሰኗ ለተሰንበት ግደይ በአምስተኛነት አጠናቅቃለች። 

Letesenbet Gidey of Team Ethiopia, gold medalist Gudaf Tsegay of Team Ethiopia, and bronze medalist Dawit Seyaum of Team Ethiopia. Source: Getty