የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝን በሉላዊ አስቸኳይ የጤና አሳሳቢነት ፈረጀ።
እንደ ድርጅቱ የማስጠንቀቂያ ደወል ዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በ75 አገራትና ግዛቶች 16,000 ያህል ደርሷል፤ የአምስት ሰዎች ሕይወቶችን ቀጥፏል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም የጤና ድርጅት በአስቸኳይ ሉላዊ ጤና ማስጠንቀቂያ የተሰጠባቸው የኮቪድ - 19 ወረርሽኝና ፖሊዮን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ያልተቋረጠ ጥረት እየተደረገበት ያለው ፖሊዮ ነው።