ኢማኑኤል ማክሮን ዳግም የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ

*** ማክሮን፤ የምርጫ ድል ውጤቱን አስመልክተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሁሉንም አካታች በሆነ ድምፀት ለድል ያበቋቸውን ደጋፊዎቻቸውን፣ ለተቀናቃኛቸው ለ ፔን ድምፅ የሰጡትንና ከቶውንም ማንንም ሳይመርጡ ድምፆቻቸውን የነፈጉትን ሁሉ አመስግነዋል።

News

France's centrist incumbent president Emmanuel Macron and his wife Brigitte Macron. Source: Getty

የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን የቀኝ አክራሪ ተቀናቃኛቸውን ሜሪን ለ ፔንን ረትተው ዳግም ተመረጡ።

የ44 ዓመቱ ፕሬዚደንት ዳግም የመመረጥ ዕድል በማግኘት ሶስተኛው የፈረንሳይ ፕሬዚደንት በመሆንም በታሪክ መዝገብ ውስጥ ሠፍረዋል። 

የምርጫ ድል ውጤቱን አስመልክተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሁሉንም አካታች በሆነ ድምፀት ለድል ያበቋቸውን ደጋፊዎቻቸውን፣ ለተቀናቃኛቸው ለ ፔን ድምፅ የሰጡትንና ከቶውንም ማንንም ሳይመርጡ ድምፆቻቸውን የነፈጓቸውን ሁሉ አመስግነዋል። 

ማንም ፈረንሳዊ ከአገሪቱ ትሩፋቶች ተቋዳሽ ሳይሆን እንዳይቀርና ፈረንሳይንም ወደ ጠንካራ አንድነት ለማምጣት ተግተው እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

የሁለተኛ ዙር ፕሬዚደንታዊ ግብራቸው ከመጀመሪያው የተለየ እንደሚሆንም ሲያመላክቱም፤

"ይህ አዲሱ ምዕራፍ ያለፉት አምስት ዓመታት ቀጣይ ሆኖ አይዘልቅም። የሚሆነው በምርጥ ፈጠራ ስብስብ ክለሳ ዘዴ የአገራችንን ወጣቶች ለተሻሉ አምስት ዓመታት ማገልገል ነው" ብለዋል። 

የተቃዋሚ ቡድን መሪዋ ለ ፔን በበኩላቸው ለመጪው የጁን የፓርላማ ምርጫ ፍልሚያቸውን በማካሔድ እንደሚዘልቁ አስታውቀዋል።                                   

 

 

 

 

 

 

 

 

 

                                                          

 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now