SKIP TO MAIN CONTENT

አብላጫ ኢትዮጵያውያን የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ ይፈልጋሉ - አፍሮባሮ ሜትር

*** የአፍሮ ባሮ ሜትር የጥናት ውጤት

Amharic News August 25, 2020
Source: Courtesy of DK

1 min read

Published

By Demeke Kebede


Skip to article content

ዛሬ ይፋ በተደረገው የአፍሮ ባሮ ሜትር 8ኛው ዙር የጥናት ውጤት ይፋ መሰረት፤

 - ከጥናቱ ተሳታፊዎች 68 በመቶዎቹ ሕገ መንግሥቱ መሻሻል አለበት ያሉ ሲሆን፥ 18 በመቶዎቹ ባለበት ቢቀጥል፤ 11 በመቶ ደግሞ በአዲስ መተካት አለበት ማለታቸውን ጥናቱ አመላክቷል።

 - ለፌዴራል መንግስት ተጨማሪ የስራ ቋንቋ ማድረግ/ማካተት በሚለው ላይም ከጥናቱ ተሳታፊዎች ውስጥ 73 በመቶዎቹ ተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎች ቢካተቱ እንደሚስማሙ  ሲገልፁ፤ 3 በመቶዎቹ ባለበት እንዲቀጥል ያሉ ሲሆን፥ 24 በመቶዎቹ ደግሞ ተቃውመውታል።

 - የጠቅላይ ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን በሁለት የምርጫ ጊዜ መገደብን በተመለከተም 68 በመቶዎቹ እንደሚደግፉት፣ 23 በመቶዎቹ እደሚቃወሙ እና 9 በመቶዎቹ ደግሞ ድምጽ አልሰጡበትም።

 - ገለልተኛ የሆነ የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት ማቋቋም የሚለውንም 55 በመቶ የደገፉ ሲሆን፥ 25 በመቶ ተቃውመውታል፤ 21 በመቶ ደግሞ ሃሳቡን ድምጽ ሳይሰጡበት ቀርተዋል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now