ቫይረስ ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ዛሬ - ሐሙስ 33 አዲስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን አስመዘገበች።
ሰባቱ ከጉዞ ተመላሽ መንገደኞች፣ ዘጠኙ መነሻው ከታውቀና በቁጥጥር ስር ከዋለ አካባቢ፣ ስድስቱ በቤት ውስጥ ምርመራ የተገኙ ናቸው።
11 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንደምን ቫይረሱ እንዳገኛቸው እየተመረመረ ነው።
በሚቀጥሉት ሶሶት ቀናት ባለ ስልጣናት 50 ፐርሰንት ያህል የሜልበርን ብሮድሜዶውስና ኪሎር ዳውንስ ቀበሌ ነዋሪዎችን ቤት ከቤት ተዘዋውሮ ለመመርመር ወጥነዋል።
ከዚያ በኋላም የ Maidstone, Albanvale, Sunshine West, Hallam, Brunswick West, Fawkner, Resevoir, እና የ Pakenham ነዋሪዎች በየቤታቸው ምርመራ ይደረግላቸዋል።
የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳን ኤል አንድሩስ ለምርመራ ዒላማ የሆኑ ቀበሌዎች ውጤት የቪክቶሪያን የቫይረስ ተዛማችነት በመቆጣጠር ረገድ ስለሚኖረው አስተዋፅዖ ሲናገሩ፤
"በእኒህ ቀበሌዎች ውስጥ ሁሉንም በቫየረሰኡ የተያዘ ሰዎች ማግኘት ከቻልን፤ በየቤታቸው ወሸባ እንዲገቡ ይደረጋል። ድጋፍም ይቸራቸዋል። በምርመራው ሳቢያ ምንም እንኳ
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍ ቢልም፤ በመተማመን መንፈስ ቫይረሱን መቆጣጠር ያስችለናል። እንዲሁም፤ በመቆጣጠር ስትራቴጂያችን ይስዘልቀናል" ብለዋል።
ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረሱ ተይዘው ካሉት ውስጥ ሁለት ሰዎች በፅኑ ሕመምተኛ ክፍሎች ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ 1000 ያህል የውስትራሊያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል እገዛ እንዲያደርጉ ወደ ቪክቶሪያ ተሰማርተዋል። 850ዎቹ በቫይረሱ ተይዘው ወሸባ የገቡትን ሰዎች ሲቆጣጠሩ፤ የተቀሩት በድርጅታዊ አቅርቦትና በሕክምና ምርመራ ዘርፍ ድጋፍ ይሰጣሉ።
እስካሁን አውስትራሊያ ውስጥ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቅቁትር 104 ደርሷል።
የኳንታስ የሠራተኛ ቅነሳ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአየር መንገድ ኢንዱስትሪ ላይ ያሳደረውን ጉዳት ተከትሎ ኳንታስ 20 ፐርሰንት ያህል ሠራተኞቹን ይቀንሳል።
ከ 30,000 ሠራተኞቹ ውስጥ 6,000ዎቹ ሥራቸውን ያጣሉ።
የሥራ ቅነሳው ሁሉንም የኳንታስ የሥራ መስኮች ይመለከታል።
በተጨማሪ 15,000 ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ላይ ተገልለው የሚቆዩ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት መጨረሻ በአገር ውስጥ በረራዎች ድጋፍ ሰጪነት ይመለሳሉ።
አየር መንገዱ ካሉት 130 አውሮፕላኖቹ ውስጥ 100 ያህሉ ለሚቀጥሉት 12 ወራት ከበረራ ውጪ ሆነው ይቆያሉ።
ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታትም የ15 ቢሊየን ዶላርስ የወጪ ቅነሳዎች ይካሄዳሉ።

