ከኤፕሪል 8 ጀምሮ ዓለም አቀፍ በረራዎች ወደ ሜልበር ይጀምራሉ

*** አንድ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ምክር ቤት አባል በወሲባዊ ጥቃት ፍጸማ ተጠርጣሪ ሆኑ

SBS Amharic

Source: Getty

ዓለም አቀፍ በረራዎች ወደ ሜልበር እንደሚጀምሩ የቪክቶሪያ መንግሥት አስታወቀ። 

በእንግሊዝ ቫሪያንት ኮሮናቫይረስ በተጠቃ አንድ የሆቴል ወሸባ ሠራተኛ ሳቢያ ሜልበርን ከተማ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ገደቦች ከተጣሉባት ወርኃ ፌብሪዋሪ ወዲህ የአየር በረራዎች ታግደው ቆይተዋል።  

ተጠባባቂ ፕሪሚየር ጄምስ ሜርሊኖ ቪክቶሪያ ለመነሻ 800 መንገደኞችን በሳምንት መቀበል እንደምትጀምርና የሆቴሎች አየር ማስተላለፊያዎች ግምገማ እንዳበቃ 1,120 መንገደኞችን በሳምንት መቀበል እንደሚቻል አስታውቀዋል።

እስካሁን ወደ አውስትራሊያ መመለስ የሚፈልጉ 36 000 አውስትራሊያውያን ባሕር ማዶ ይገኛሉ።

የወሲብ ጥቃት ተጠርጣሪ የምክር ቤት አባል

 

 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር ግላዲስ በርጂክሊያን የናሽናልስ ፓርቲ ምክር ቤት አባል ማይክል ጆንሰን በአንዲት የወሲብ ሠራተኛ ላይ ወሲባዊ ጥቃት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጣሪ መሆን ያስደነገጣቸው መሆኑን ተናገሩ።

ወ/ት በርጂክሊያን ጉዳዩን ፓርላማ ውስጥ ከመስማታቸው በፊት ስለ ጉዳዩ ምንም የሚያውቁት እንዳልነበረም ጠቅሰዋል። 

የጆንሰንን ስም ሳይጠቅሱ ይህን ጉዳይ ፓርላማ ውስጥ ለአደባባይ ያዋሉት የሌበር የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ትሪሽ ዶይል ናቸው። 

አቶ ጆንሰን በወሲባዊ ጥቃት ተጠርጣሪ መሆናቸውን ተከትሎ ከፓርላማ ጸሐፊነት ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቅቀዋል። ተጠርጣሪነታቸውን አስመልክቶ በገዛ ፍላጎታቸው ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ፖሊስ ጋር መነጋገራቸውን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።  

አቶ ጆንሰን በነገው ዕለት ፖሊስ ዘንድ ቀርበው በይፋ የምርመራ ቃላቸውን ይሰጣሉ።  

ወሲባዊ ጥቃትን አስመልክቶ መረጃ ወይም ድጋፍ የሚሹ ከሆነ በ 1-800 RESPECT ወይም 1800 737 732 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የካቢኔ ሹም ሽር

 

 

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክርስቲያን ፖርተርና የመከላከያ ሚኒስትር ሊንዳ ሬይኖልድስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ እየደርሱ ባሉ ጫናዎች ሳቢያ በሚያደርገው ሹም ሽር ይዘውት ካሉት ሚኒስትራዊ ኃላፊነታቸው እንደሚነሱ ይጠበቃል።

በሹም ሽሩም ሚካዬላ ካሽ በፖርተር እግር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፤ ፒተር ዳተን በሬይኖልድስ ምትክ የመከላከያ ሚኒስትር ኃላፊነቶችን እንደሚረከቡ እየተነገረ ይገኛል።

 

 

 

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now