ዋትስኧፕ በበርካታ አገራት ውስጥ የመልዕክት አገልግሎቱ ለጊዜው ይህ ነው ተብሎ ባልተገለጠ ሁኔታ ተቋርጧል።.
ኧፑ እስካሁን ለተጠቃሚዎቹ ባለማቋረጥ "connecting" የሚል መልዕክት ከማሳየት በስተቀር መልዕክቶችን የመቀበልና የማስተላልፍ አገልግሎቱን እየሰጠ አይደለም።
የዋትስኧፕ ወላጅ ኩባንያ ሜታ ሁነቱን የተረዳ መሆኑንና ችግሩንም ለመክላት እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።
ችግሩ ከገጠማቸው አገራት ውስጥ አውስትራሊያ፣ እንግሊዝ፣ ሕንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ፈረንሳይና ሌሎች አገራት ይገኙበታል።
ዋትስኧፕ ከ180 በላይ አገራት ውስጥ ከሁለት ቢሊየን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት።