ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ መንግሥታቸው ምጣኔ ሃብታዊ ኃላፊነት የተላበሰና የምርጫ ቃል ኪዳኖቹን ሙሉ በሙሉ የሚፈፅም እንደሚሆን አስታወቁ

*** የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቶኪዮ መልስ ወደ ፊጂ አቀኑ፤ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከስምንት የኢንዶ ፓስፊክ አገራት መሪዎች ጋር ለመነጋገር የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ከሰለሞን ደሴቶች ጀምረዋል።

News

Australian Prime Minister Anthony Albanese. Source: Getty

ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ መንግሥታቸው ምጣኔ ሃብታዊ ኃላፊነት የተላበሰና የምርጫ ቃል ኪዳኖቹን ሙሉ በሙሉ የሚፈፅም እንደሚሆን አስታወቁ። 

አቶ አልባኒዚ ከብሔራዊ ባንክ ገዢና በጅሮንድ ጂም ቻልመርስ ጋር በምጣኔ ሃብት ዙሪያ ከተነጋገሩ በኋላ የወለድ መጠን እንደሚጨምርና የምጣኔ ሃብት ዕድገት ላይም ተፅዕኖ እንደሚኖረው እርግጠኛ መሆናቸውን ገልጠዋል። 

አያይዘውም፤ መንግሥታቸው ብርቱ የሆነ ምጣኔ ሃብታዊ ተግዳሮቶች እንደተጋረጡበትና ያለፈው መንግሥት በይፋ ከገለጣቸው ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ የከፋ መሆኑን አመላክተዋል። 

ሆኖም መንግሥት ወጪ ከሚያደርጋቸው ሙዋዕለ ንዋይ ፈሰሶቹ ካለፈው መንግሥት በተሻለ ለግብር ከፋዮች ትሩፋቶችን እንደሚያስገኝ ገልጠዋል።   

እስያ ፓስፊክ

አዲሱ የፌዴራል መንግሥት ባለፉት መሪዎች የተፈፀሙትን ስህተቶች ከፓስፊክ ደሴት አገራት ጋር ያሉ ግንኙነቶችን በመጠገን ለማደስ እንደሚጥር አመለከተ። 

ይህንንም ግብር ላይ ለማዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ ዛሬ ወደ ሐሙስ ወደ ፊጂ ተጉዘው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፍራንክ ናህኒማህራህማና ገዲብ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ።

News
Australia's Foreign Minister Penny Wong. Source: Getty

ፊጂ እያሉም አውስትራሊያ ለቀጣናው ልታስገኝ የምትችላቸውን አዲስ ትሩፋቶች ይፋ ያደርጋሉ። 

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የቻይና በኢንዶ-ፓስፊክ ዙሪያ ባሳየችው ፍላጎት ሳቢያ በተለይም ከሰለሞን ደሴቶች ጋር የተዋዋለችው የፀጥታ ስምምነት ውጥረትን ፈጥሯል። 

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ትናንት እኩለ ለሊት ላይ ሰለሞን ደሴቶች ገብተዋል። 

በቆይታቸውም ወቅት ከሰለሞን ደሴቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ገዲብ ባለ ስልጣናትና ጠቅላይ ሚኒስትር ሳጎቫሬ ጋር ይነጋገራሉ።

News
Chinese Foreign Minister Wang Yi. Source: Getty

ሚኒስትሩ በቀጣይነትም ከኪሪባቲ፣ ሳሞኣ፣ ፊጂ፣ ቶንጋ፣ ቫኑኣቱ፣ ፓፑዋ ኒው ጊኒና ቲሞር ሌስቴ መሪዎች ጋር ተገናኘተው በልማትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ።


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now