የቪክቶሪያ ጤና ሚኒስትር ጄኒ ሚካኮስ በአዕምሮ ጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ ሊተኩ ነው

*** የቪክቶሪያ ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ ቁጥር ወደ 12 ወረደ

Amharic News 26 September 2020

Victorian mental health minister Martin Foley will replace Jenny Mikakos as health minister after she resigned from the position Source: AAP

የቪክቶሪያ ጤና ሚኒስትር ጄኒ ሚካኮስ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በሆቴል የኮሮናቫይረስ ወሸባ ፕሮግራም መርማሪ ቦርድ ዘንድ ቀርበው ለተፈጸመው ስህተት ተጠያቂዋ ሚኒስትሯ ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ ከፓርላማና ከሚኒስትር ማዕረጋቸው እንደሚለቁ አስታውቀዋል። 

የሆቴሉ የኮሮናቫይረስ ወሸባ ፕሮግራም ቪክቶሪያ ውስጥ ለተከሰተው የሁለተኛ ዙር የኮቨድ - 19 ማገርሸት አንዱ ሰበብ ተደርጎ ተወስዷል።

ሚኒስትር ሚካኮስ በዛሬው ዕለት ለቪክቶሪያ እንደራሴ ከዛሬ ጀምሮ ከሚኒስትርነት ኃላፊነታቸው የለቀቁ መሆናቸውን የሚያሳውቅ የመልቀቂያ ደብዳቤ መጻፋቸውንና ከፓርላማም እንደሚሰናበቱ ገልጠዋል።

ሚኒስትሯ "ከቶውንም ያልተገባደደ ሥራን መተው አልሻም። ይሁንና ፕሪሚየሩ ለመርማሪ ቦርዱ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደ እውነቱ ከሆነ እኔ በብርቱ የማልስማማባቸው ጉዳዮች ስላሉ በእሳቸው ካቢኔ ውስጥ ሆኜ ግልጋሎቴን መቀጠል አልችልም" ብለዋል።

ፕሪሚየር አንድሩስ የሚኒስትሯን ስንብት በእጅ ስልክ የፅሑፍ መልዕክት እንዳወቁ ጠቅሰው፤ የሚኒስትሯን በፈቃዳቸው መሰናበት 'ተገቢ ድርጊት' ነው ብለዋል። 

የአዕምሮ ጤና ሚኒስትሩ ማርቲን ፎሊ በእግራቸው እንደሚተኩም ተገልጧል። 

ኮቨድ - 19 - ቪክቶሪያ 

ቪክቶሪያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ተዛማችነት ማሽቆልቆሉን ቀጥሎ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 12 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ የአንድ ሰው ሕይወት ተቀጥፏል።

የአንዱን ሰው ሕልፈተ ሕይወት አክሎ ቪክቶሪያ ውስጥ 782 በመላው አውስትራሊያ 870 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

የሜልበርን የ14 ቀናት የቫይረሱ መስፋፋት አማካይ መጠን በዛሬው ዕለት 23.6 ሲሆን በሪጂናል ቪክቶሪያ 0.8 ደርሷል። 

 


1 min read

Published

Updated

By NACA


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now