የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከሐሙስ አንስቶ መቀሌ በመዝለቅ መደበኛ ኃላፊነቱን መወጣት ይጀምራል

የመከላከያ ሠራዊቱ ግዳጅ አፈፃፀም በፌዴራል መንግሥቱና ሕወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን የሚወጣ እንደሚሆን ተነግሯል።

Redwan Hussien.jpg

Redwan Hussien, Minister, National Security Advisor to the PM of FDRE. Credit: Erhan Elaldı/Anadolu Agency via Getty Images

የሠራዊቱን ወደ መቀሌ ዘልቆ ግዳጅ ላይ የመሠማራቱን ተግባር በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረጉት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስት ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን ናቸው።

አቶ ሬድዋን በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራው ልዑክ ቡድን አባል ሆነው በትናንትናው ዕለት መቀሌ ደርሰው ተመልሰዋል።

የልዑኳን ቡድኑም ከመቀሌ መልስ የጉዟውን ሂደት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስረዳቱን የገለጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ተጀምረው በትግበራ ላይ ያሉ አገልግሎቶች ተፋጥነው እንዲቀጥሉ መመሪያ መስጠታቸውንም አክለው ገልጠዋል።

በመመሪያው መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነገው ዕለት አቋርጦ የነበረውን የመቀሌ በረራ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቀጥል ሲሆን፤ ሌሎችም አገልግሎት ሰጪዎች የየድርሻ ተግባራቶቻቸውን አፋጥነው የሚቀጥሉ ይሆናል።


1 min read

Published

By Stringer Report

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now