በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ የማክሰኞው ብሔራዊ በጀት ለአውስትራሊያውያን ቤተሰቦች የኑሮ ውድነትን የሚቀርፍ እንደሚሆን ገለጡ

*** ሌበር የኑሮ ውድነቱ ጫና አስባብ በአብዛኛው ለአንድ አሠርት ዓመታት ያህል በክሽፈት የተመላው የቅንጅት መንግስቱ ፖሊሲ ነው ሲል አመላከተ

News

Treasurer Josh Frydenberg. Source: Getty

የፌዴራል በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ የማክሰኞው ብሔራዊ በጀት ለአውስትራሊያውያን ቤተሰቦች የኑሮ ውድነትን የሚቀርፍ እንደሚሆን ገለጡ።

አቶ ፍራይደንበርግ የበጀት መስፈርቶቹ ንሮ ባለው የዋጋ ግሽበት ተጨማሪ ንረትን የሚፈጥርና ብሔራዊ ባንክን ለወለድ መጠን ጭማሪ ግድ የሚያሰኝ አለመሆኑን ተናግረዋል። 

በጅሮንዱ ከ S-B-S ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የበጀት ወለሉ መልካም ሁኔታ ላይ እንዳለ ቢጠቁሙም የነዳጅ ቀረጥን መግታትን፣ የዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የግብር ቅናሽ ይደረግ እንደሁ ግና መግለጥ አልፈቀዱም። 

ይሁንና በሌላ በኩል የሌበሩ ጂም ቻልመር ከ A-B-C ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የኑሮ ውድነቱ ጫና አስባብ በአብዛኛው ለአንድ አሠርት ዓመታት ያህል በክሽፈት የተመላው የቅንጅት መንግስቱ ፖሊሲ ነው ሲሉ አመላክተዋል።                                                         

ባይደን ዩክሬይን

ዋይት ሐውስ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ፖላንድ ላይ የሩስያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን "ስልጣን መቆየት አይችሉም" ሲሉ የተናገሩትን አስመልክቶ ማብራሪያ ለመስጠ ተገድዷል።

በማብራሪያውም የባይደን የፖላንድ መዲና ዋርሶ ንግገር ፑቲን ዩክሬይን ውስጥ "ስትራቴጂያዊ ክሽፈት" ገጥሟቸዋል ማለታቸው እንደሆነ አቃንቶ ገልጧል።

የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናትም ፕሬዚደንት ባይደን "የመንግሥት ለውጥ" ጥሪ ማቅረባቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል። 

ክሬምሊን ግና በሩስያ የውስጥ ጉዳይ መወሰን "የባይደን ድርሻ አይደለም" ሲል የአፀፋ ምላሽ ሰጥቷል።   

 

 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now