SKIP TO MAIN CONTENT

ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ 184 ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው

*** የፌደራል ሥነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን

ACC
Source: Courtesy of FEAACC

1 min read

Published

By Demeke Kebede


Skip to article content

የፌደራል ስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ያልሆኑ 184 ባለስልጣናት በወንጀል እንዲከሰሱ ስም ዝርዝራቸውን ለፌደራል ፖሊስ መስጠቱን ለአል ዐይን አማርኛ  ገልጿል፡፡

ሀብትና ንብረታቸውን ማስመዝገብ ያለባቸው የመንግስት ሹመኞች  በተደጋጋሚ እንዲያስመዘግቡ ቢጠየቁም ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

ኮሚሽኑ ባለስልጣናቱ ሀብታቸውን እንዲያስቀምጡ ያስቀመጠው ቀነገድብ ባለፈው ሀምሌ 30 ለሁለተኛ ጊዜ በማለፉ ምክንያት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድርጉን ገልጿል፡፡

በቀነገደቡ ማስመዝገብ ያልቻሉ 184 የፌደራና የአዲስ አባባ መገኘታቸውንና እነሱም በህግ ይጠየቃሉ ብሏል ኮሚሽኑ፡፡ ኮሚሽኑ የባለስልጣናቱን ስም ዝርዝር ግን ይፋ አላደረገም፡፡

በ2002 ዓ.ም በተወካዮች ምክርቤት በወጣው አዋጅ መሰረት ባለስልጣናት ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ያስገድዳል፡፡


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now