በኪንግ ሪችድ (የቴኒስ ኮከቦቹ ቬኑስና ሴሬና ዊልያምስ አባት) የሕይወት ታሪክ ፊልም ትወና የ94ኛው ኦስካር ምርጥ መሪ ተዋናይ ሽልማት አሸናፊ ለመሆን የበቃው ዊል ስሚዝ የመድረክ አጋፋሪ ክሪስ ሮክን በጥፊ በመምታቱ ይቅርታ ጠይቋል።
ስሚዝ የኦስካር አሸናፊነቱ ይፋ ከመሆኑ በፊት ሮክ ባለቤቱን ጃዳ ፒንኬት ስሚዝን ስም አንስቶ ቀልድ በመሰንዘሩ ተናድዶ መድረክ ላይ በመውጣት በጥፊ ተማትቷል።
የኦስካር ሽልማቱን ሲቀበል ንግግር ባደረገበት ወቅት "ሪችድ ዊልያምስ የቤተሰቡ ብርቱ ተከላካይ ነው" ነው ብሏል።

አያይዞም "የፍቅር መርከብ መሆን እሻለሁ። በታሪካቸው ላይ እምነት ለጣሉብኝ ቬኑስና ሴሬና ለመላው የዊሊያምስ ቤተሰብ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ። ማድረግ የምሻው ያንን ነው፤ እንዲያ ላለ ፍቅር፣ ክብካቤና ስጉነት አምባሳደር መሆን እሻለሁ።
"እብድ አባት እመስላለሁ። ይሁንና ፍቅር የእብደት ነገሮችን ያሠራል።
"ለአካዳሚው ይቅርታ ማቅረብን እሻለሁ፤ አብረውኝ በዕጩነት ለቀረቡ ሁሉ ይቅርታን እጠይቃለሁ" ብሏል።
ዩክሬይን ሩስያ
የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከኑክሊየር ነፃ ዩክሬይንን አካትቶ የሩስያን የፀጥታ ዋስትናዎችን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆናቸውን ገለጡ።
አቶ ዜሌንስኪ ለተጨማሪ ዋስትናዎች የቡዳፔሽት ዓይነት የደኅንነት ዋስትና ሰነድ እንዲዘጋጅ እንደሚሹም አሳስበዋል።
የዩክሬይን ፕሬዚደንት ማናቸውም ዓይነት ስምምነት ላይ ለመድረስ ከሩስያ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በአካል መገናኘት እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።

