ይህም የዓለም ዋንጫን ለመመልከት ወደ ዶሃ ለሚያቀኑ የስፖርት አፍቃሪዎች የጤና ዘርፍ ውጣ ውረድ ማቃለያ ተደርጎ በመልካም ጎንነት ተወስዷል።
በኳታር አስተናጋጅነት የሚካሔደው የዓለም ዋንጫ ከኖቬምበር 20 እስከ ዲሴምበር 18 ይከናወናል።
ኳታር ከመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያዋ የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ አገር ናት።
የዓለም ዋንጫ አስተናጋጇ አገር ውስጥ በቀን 470 ሰዎች ያህል በኮቪድ-19 የሚጠቁ ሲሆን ዕለታዊ የሞት መጠን በአማካይ 0.14 እንደሁ ተመልክቷል።
የአውስትራሊያ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾችን ጨምሮ የኳታርን ሰብዓዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ ከየአቅጣጫው ብርቱ ትችቶች እየተሰነዘሩባት ይገኛል።