እጅግ የላቀ ስኬት ያስመዘገበው ብላክ ፓንዘር ፊልም ዋና ተዋናይ ቻድዊክ ቦዝማን በኮሎን ካንሰር ሳቢያ በዛሬው ዕለት ሕይወቱ አልፋለች።
ቦዝማን ምንም እንኳ በአደባባይ ባይናገርም ሕመሙ እንዳጠቃው ያወቀው በ2016 ባካሔደው የሕክምና ምርመራ ወቅት ነበር።
የቦዝማን ሕይወት ያለፈው ሚስቱና ቤተሰቡ ከጎኑ ሆነው በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ነው።
በ2018 ለዕይታ የበቃው ብላክ ፓንዘር ፊልም የተሠራው አፍሪካ ውስጥ ባለችና ሉዓላዊነቷን ባላስደፈረችው 'ዋካንዳ' የልብ ወለድ አገር በመሆኑ ተምሳሌነቷ ከኢትዮጵ ጋር ተያይዞ በወቅቱ ሰሞነኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
ቻድዊክ ቦዝማን በዋና ተዋናይነት የተወነበት ብላክ ፓንዘር ፊልም በአያሌ ሃያሲያንና ተመልካቾች ዘንድ ከፍ ያለ አድናቆትን ያገኘ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ AUD$1.3 ቢሊየን ገቢ አስገኝቷል።
ቫይረስ - ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ከጁላይ 5 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ100 በታች ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ ቁጥር አስመዝግባለች።
በዛሬው ዕለት ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 94 ሲሆን 18 ሕይወታቸውን አጥተዋል።
እስካሁን ድረስ በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር በስቴት ደረጃ 514 በአገር አቀፍ 601 ደርሷል።
የቫይረሱ መስፋፋት ከ100 በታች መውረድ ከ 8pm እስከ 5am ያለውን የሰዓት ዕላፊ ገደብ ጨምሮ የደረጃ አራት ገደቦችም ይላላሉ የሚል ተስፋ ቢያጭርም፤ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ ግና በፍጥነት ገደቦችን ለማላላት እንደማይጥደፉ አስታውቀዋል።
አያይዘውም "የሁለተኛ ዙር ወረርሽኙን በውል ድል ልንነሳ እንሻለን፡፤ ይህም ማለት ሶስተኛ ዙር ወረርሽኝን ማስወገድ እንችላለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ከዛሬና ነገ ፀሓያማ አየር ንብረት ጋር ተስታኮም ቪክቶሪያውያን የኮሮናቫይረስ ገደቦችን እንዳይጥሱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

