የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትና የቻይና ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ አምስተኛ የመሪዎች ንግግር አደረጉ።
ንግግሩ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተካሔደው በስልክ ሲሆን፤ የታይዋንና ዩከሬይ ጉዳዮች ከመነጋገሪያ አጀንዳዎቻቸው ውስጥ ተካትተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲን ታሳቢ የታይዋን ጉብኝት "በእሳት መጫወት" እንደሚሆን ጠቅሰው የቻይናው ፕሬዚደንት ሺ ፕሬዚደንት ባይደንን ልብ ማሰኘታቸው ተነግሯል።
የመሪዎቹን የስልክ ንግግር አስመልክቶ የቻይና የመንግሥት ብዙሃን መገናኛ አቶ ሺ ለአቶ ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ ከ"አንድ ቻይና መርህ" እንዳታልፍ፣ ቻይና የታይዋይንን ራሷን የቻለች አገር የመሆን ዕሳቤና የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንደምትቃወም በአፅንዖት መግለጣቸውን አስታውቋል።

Concerns are mounting over a possible visit to the Taiwain by US House Speaker Nancy Pelosi. Source: AAP, AP / J. Scott Applewhite
አያይዞም ፕሬዚደንት ሺ፤
"በእሳት የሚጫወቱ ቃጠሎ ያገኛቸዋል"
"[እኛ] ዩናይትድ ስቴትስ ይህን አጥርታ ትመለከታለች የሚል ተስፋ አለን" በማለት ለባይደን ማመላከታቸውን አስፍሯል።
ሆኖም በዋይት ሃውስ በኩል አቶ ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ የ"አንድ ቻይና" ፖሊሲዋን እንዳልቀየረች ለቻይናው ፕሬዚደንት ያሳሰቡ መሆኑ፣ በታይዋን ሰርጥ አካባቢ ሰላምና መረጋጋት እንዳይደፈረስ የምትሻ መሆኑንም ግልፅ ማድረጋቸውንና ንግግሩም ከሁለት ሰዓታት በላይ መፍጀቱን ገልጧል።
በዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት በኩል አቶ ባይደን ባለፈው ወርሃ ማርች የአራተኛው ዙር የመሪዎች ንግግር ወቅት ሩስያ ለምታካሂደው የዩክሬይን ጦርነት የቁሳቁስ ድጋፍ እንዳታደርግ ቻይናን ማስጠንቀቃቸውንና እስካሁንም ቻይና ያንን ቀይ መስመር አላለፈችም በማለት አመላክተዋል።

Source: Biden
የአፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲ ቢሮ የታይዋን ጉብኝታቸውን አስመልክቶ ይፋ መግለጫ አልሰጠም።
ባለፉት ጊዜያት በዩናይትድ ስቴትስ አፈ ጉባኤ የታይዋን ጉብኝት የተካሔደው በ1977 ኒዊት ጊንጊሪች አፈ ጉባኤ በነበሩበት ወቅት ነው።
የመብራት ዋጋ
የኃይል ምንጭ ዋጋ ከፍተኛ ማሻቀብ እንደሚያደርግ ግምት ውስጥ በማስገባት፤ አውስትራሊያውያን የመብራት ክፍያቸው ሊንር እንደሚችል ተነገረ።
የአውስትራሊያ የኃይል ገበያ ኦፕሬተር በወርሃ ጁን የጅምላ የኃይል ዋጋ በሜጋዋት $264 መድረሱን አስታውቋል።
ባለፉት ሶስት ወራት የኃይል ዋጋ ጭማሪ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በ203 ፐርሰንት መናሩ ተመልክቷል።