በየዓመቱ የዘመን መለወጫ ዋዜማ ቅበላ የአውስትራሊያ ዓለም አቀፍ ገፅታ ሆና ያለችው ሲድኒ የዘንድሮው የ2023 የዘመን ቅበላ ፓይሮቴክኒንክ ርችት ተኩስ ካምናው በእጅጉ 'የገዘፈና የደመቀ' እንደሚሆን አስታወቀች።
የሲድኒ ወደብ ድልድይ ምሽት ፕሮግራሙ የሚጀምረው ከ7:30 pm በነባር ዜጎች ጢስ ማጠን ሥነ ሥርዓት ይሆናል።

በዋዜማው ምሽት ከነባር ዜጎች 'እንኳን ወደ አገራችን መጣችሁ' አቀባበል ሥነ ሥርዓትን አካትቶ የተለያዩ የሙዚቃና የመብራት ትዕይንቶች ይቀርባሉ።
ሜልበርን
የመጀመሪያው የቤተሰብ የአዲስ ዓመት ቅበላ ርችት የሚተኮሰው 9:30 pm ላይ ይሆናል።
ዶክላንድስ፣ ፍላግ ስታፍ ጋርደንስ፣ ኪንግስ ዶሜይንና ትሬዠሪ ጋርደንስ የተለያዩ የመዝናኛ ትዕይንቶች የሚቀርቡባቸው ዋነኛ የአዲስ ዘመን መቀበያ ዞኖች ሆነው ተደልድለዋል።
ዝግጅቶቻቸውን የሚጀምሩት ዲሴምበር 31 ቅዳሜ ከ6:00 pm አንስቶ ሲሆን የሚጠናቀቀውም ጃኑዋሪ 1 እሑድ 1:00 am ይሆናል።

ከዋነኛ አራት ዞኖች ባሻገርም በፉትስክሬይ ፓርክ፣ ዳዲኖንግ ፓርክ፣ ጂሎንግ ዎተርፍሮንት እና ፖርታርሊንግተን የርችት ተኩሶች ይካሔዳሉ።
የሕዝብ ትራንስፖርት
ሁሉም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች ከቅዳሜ ምሽት 6:00 pm እስከ እሑድ ጃኑዋሪ 6:00 am በነፃ ለሕዝብ አገልግሎትን ይሰጣሉ።
ዋነኛዎቹን ጎዳናዎች ጨምሮ በርካታ የሜልበርን ከተማ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናሉ።
ሱቆች
ዉልዎርዝ እና ኮልስን አካትቶ በርካታ ትላልቅ የገበያ አዳራሾች ጃኑዋሪ 1 ከጠዋቱ 8:00 am አንስተው ለሸማቾች ግልጋሎቶቻቸውን ይሰጣሉ።
እንዲሁም ቻድስተን፣ ሜልበርን ሴንትራል፣ ሃይፖይንት እና ዶንካስተር የገበያ ሾች ከከ10:00 am ጀምሮ ክፍት ይሆናሉ።

