በአውስትራሊያ ሁለት ትላልቅ ከፍለ አገራት ውስጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ 72 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ኒው ሳውዝ ዌይልስ 52 ቪክቶሪያ 20 ነዋሪዎቻቸው በኮቪድ-19 ተጠቅተው ለሕልፈተ ሕይወት መዳረጋቸውን አስታውቀዋል።
እንዲሁም፤ ባለፉት 24 ሰዓታት ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 13,524 በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ ሆስፒታል ካሉ 2,663 ሕሙማን ውስጥም 182 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
በሌላም በኩል ቪክቶሪያ 10,589 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተውባታል። ከ 889 የሆስፒታል ሕሙማኖቿ ውስጥ 111ዱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
እንግሊዝ ዩክሬይን
የሩስያን በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሠራዊት ወደ ዩክሬይን ድንበር ማስጠጋት ተከትሎ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የአውሮፓን ድንበር ለማጠናከር የኔቶ አካል የሆነውን የእንግሊዝ ጦር ቁጥር በእጥፍ ከፍ ለማድረግ አስበዋል።
በሚቀጥለው ሳምንትም ወደ ሪጁኑ ተጉዘው ጉብኝት ያደርጋሉ፤ እንዲሁም ከሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ይነጋገራሉ።
ተመድ ሉናር አዲስ ዓመት
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ለቻይናውያንና በዓሉን በተለያዩ አገራት ለሚያከብሩ ሁሉ የሉናር አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን አስተላለፉ።
አክለውም የቻይና መንግሥት ለተባበሩት መንግሥታት ያደረገውን አስተዋፅዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በቅርቡ በሚከፈተው የቤጂንግ የክረምት ኦሎምፒክ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደሚገኙም ገልጠዋል።

