"የአማራ ሕዝብ በቀል ለመበቀል አልተዘጋጀም፤ "ሂሳብ እናወራርዳለን" ባዮችን በዝምታ አይታገስም" የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ

*** "ከ942 የምርጫ ክልል ውጤት ሰነዶች መካከል እስካሁን የ618ቱ ውጤት ደርሶናል" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Mekelle, Ethiopia.

Mekelle, Ethiopia. Source: Getty

የብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ትሕነግን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በፀረ አማራ ጥላቻ ነዢነት ኮንኗል።

በመግለጫው የትሕነግ አመራሮች "በተግባር ፈጽሞ የማይሳካ ቢሆንም በፕሮፖጋንዳ ደረጃ ዛሬ "ሂሳብ እናወራርዳለን" " የሚል ዕሳቤ አላቸው ሲል ጠቁሞ ሆኖም "የአማራ ሕዝብ የትኛውንም በቀል ለመበቀል ፍፁም አልተዘጋጀም። ይህ ማለት ግን "ሂሳብ እናወራርዳለን" ባዮችን በዝምታ ይታገሳል ማለት አይደለም" ብሏል።

አያይዞም "ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ በራሳቸው መስዋትነት ነፃነታቸውን ያስከበሩ የአማራ አካባቢዎች መሆናቸውን በድጋሚ እናሳውቃችኋለን" ሲል ከሶስት አሠርት ዓመት በላይ የይገባኛል ጥያቄ ይዞ ያለውን የአካባቢ ጉዳይ ላይ አፅንዖት ሰጥቶ አቋሙን ገልጧል።

በሌላ በኩል ባለፈው ሰኞ ምሽት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው የተናጠል ተኩስ አቁም ስምምነት "የኢትዮጵያ መንግሥት ሁሉም የፌዴራል እና የክልል ሲቪልና ወታደራዊ ተቋማት፣ ከመንግሥት በሚሰጣቸው ዝርዝር አፈጻጸም መሠረት በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም እንዲያከብሩ እና እንዲያስከብሩ" መታዘዛቸውንና “ይሄን መልካም ዕድል ለክፉ የሚጠቀሙ ወገኖች ካጋጠሙ ግን አስፈላጊው ሕግን የማስከበር ተግባር እንደ አግባቡ የሚከናወን ይሆናል”  ሲል አስጠንቅቋል።

የትሕነግ አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በፊናቸው ባለፈው ማክሰኛ "100 ፐርሰንት መቀሌን ተቆጣጥረናል። ጦራችን በደቡብና በምሥራቅ እያሳደደ ነው፤ ከግዛታችን አንዲት ኢንች እንኳ ሳትቀር ጠላትን እስከምንከላ ድረስ እንቀጥላለን" ሲሉ ለሮይተርስ ገልጠዋል። 

የምርጫ 2013 ውጤት 

በአጠቃላይ ምርጫው ከተካሄደባቸው 942 የምርጫ ክልሎች መካከል እስካሁን የ618 የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ማዕከል መድረሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ተናግረዋል።

ወ/ሪት ብርቱካን በ6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ውጤት አሰባሰብ ሂደት እና በሂደቱ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ "በጥቅሉ ለቦርዱ እንዲደርሰው የሚጠበቀው የ942 የምርጫ ክልሎች ውጤት ነው፡። ከዚህ ውስጥ እስካሁን የ618 የምርጫ ክልሎች ውጤት ደርሶናል።" ብለዋል ሰብሳቢዋ።

በ160 የምርጫ ክልሎች ላይም የተለያዩ ፓርቲዎች የቅሬታ አቤቱታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ ሰብሳቢዋ ከአቤቱታዎቹ ከፊሉ በተደራጀ መልኩ የቀረቡ ባለመሆናቸው ይኸው ተስተካክሎ እንዲቀርብ ለፓርቲዎች ጥሪ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]

 


2 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now