ኢትዮጵያ ለብሪክስ አባልነት ጥያቄ አቀረበች

ኢትዮጵያ ለብሪክስ አባልነት ማመልከቻ ማስገባቷንና ለአዎንታዊ ምላሽም ተስፋ እንዳላት የገለጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ናቸው።

Brics.jpg

Credit: BRICSSA

የኢትዮጵያን የአባልነት የብሪክስ አባልነት ጥያቄ ማቅረብ የገለጡት የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያ እንደ አፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት አኅጉራዊና ሉላዊ ድርጅት መሥራች አባልነቷና ለብሔራዊ ጥቅሞቿም ዋስትና ለማስገኘት ለብሪክስ አባልነት ማመልከቻዋን ማስገባቱ ጠቃሚ ፋይዳ እንዳለው አመላክተዋል።

ምላሹም አዎንታዊ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል።

በእንግሊዝኛው ምሕፃረ ቃል ብሪክስ ተብሎ የሚጠራው በብራዚል፣ ሩስያ፣ ሕንድ፣ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ የተዋቀረው በማደግ ላይ ያሉ አገራት የምጣኔ ሃብት ትብብር ቡድን ከኢትዮጵያ ቀደም ብሎ ከበርካታ አገራት የአባልነት ጥያቄዎች ቀርበውለታል።

በኬፕ ታውን ደቡብ አፍሪካ ግንቦት 24 እና 25 ለሁለት ቀናት የብሪክስ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትሮች ስብሰባ ባካሔዱበት ወቅት ከአፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ እስያ ፓስፊክና ደቡብ አሜሪካ የተውጣጡ ወደ 20 የሚጠጉ አገራት የአባልነት ማመልከቻ ማስገባታቸው ተነግሯል።
የአዲስ አባልነት አመልካቾች ጥያቄም በደቡብ አፍሪካ ሳንድተን ኮንቬንሽን ማዕከል ጆሃንስበርግ ከተማ ከኦገስት 22 እስከ 24 ቀን 2023 በሚካሔደው 15ኛው የብሪክስ ጉባኤ ወቅት የሚወሰን ይሆናል።

Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service