SKIP TO MAIN CONTENT

ሊብራልና ናሽናልስ ፓርቲዎች አዲስ መሪዎችን መረጡ

*** ሱዛን ሊ የሊብራል ፓርቲ፤ ፔሪን ዴቪ የናሽናልስ ፓርቲ ምክትል መሪ ሆነው ተመርጠዋል።

News
Newly elected Leader of the Liberal Party Peter Dutton (L), and Newly elected Nationals leader David Littleproud (R). Source: AAP

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

የቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር ፒተር ዳተን ያላንዳች ተቀናቃኝ የሊብራል ፓርቲ መሪ ሆነው ተመረጡ።

 

ፓርቲው የቀድሞዋን የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ሱዛን ሊ ያለ ተቀናቃኝ በምክትል መሪነት መርጧል። 

 

የሁለቱን አዲስ የፓርቲ መሪዎች ምርጫ አስመልክቶ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የሊብራል ፓርቲ መሪ ስኮት ሞሪሰን ተመራጮቹ በቂ ተሞክሮ ያላቸው እንደሆኑና ሙሉ ድጋፋቸውንም እንደሚሰጧቸው ተናግረዋል። 

 

በሌላም በኩል የናሽናልስ ፓርቲ ዴቪድ ሊትልፕራውድን በመሪነት ፔሪን ዴቪን በምትል መሪነት መርጧል። 

News
Newly elected Nationals Deputy Leader Perin Davey and newly elected Nationals leader David Littleproud. Source: AAP

ለናሽናልስ ፓርቲ መሪነት ከሊትልፕራውድ ሌላ በለስ ባይቀናቸውም የቪክቶሪያ ናሽናልስ ምክር ቤት አባል ዳረን ቸስተር የቀድሞውን የፓርቲ መሪና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተቀናቅነው ለውድድር ቀርበዋል።  

 

አአቶ ዴቪድ ሊትልፕራውድ የናሽናልስ ፓርቲ መሪ ሆነው መመረጣቸውን አስመልክተ ሲናገሩ "በሙያዊ ሕይወታቸው ውስጥ ከፍተኛ ክብር የተሰማቸው ቀን" እንደሆነ ተናግረዋል። 

 

 

የናሽናልስ ፓርቲ መሪ ምርጫ ከመካሔዱ በፊት ባርናቢ ጆይስ ከቻናል 7 ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሊብራል ፓርቲ 19 የምክር ቤት ወንበሮችን ሲያጣ ፓርቲያቸው ግና  በእሳቸው አመራር ከአገራዊ ምርጫው በፊት ይዟቸው የነበሩትን የምክር ቤት ወንበሮች ሙሉ በሙሉ እንዳስመረጠ ገልጠዋል። 

 

 

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now