የቀድሞው የሶቪየት ኅብረት ፕሬዚደንት ሚኻይል ጎርቫቾብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ የቀዝቃዛውን ጦርነት እንዲያከትም አድርገው ሶቭዬት ኅብረትን ከመበተን መታደግ የተሳናቸው የቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት ፕሬዚደንት ሚኻይል ጎርቫቾቭ በ91 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሩሲያ ዜና ኤጀንሲዎች አስታወቁ። 1 min read
Published 31 August 2022 8:20am
By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS
Skip to article content Share this with family and friends
የመጨረሻው የሶቭዬት ኅብረት ፕሬዚደንት ጎርቫቾቭ ከዩናይትድ ስቴጽ ጋር የጦር መሳሪያዎች ቅነሳና አውሮፓን ለሁለት ከፍሎ የነበረው የበርሊን ግንብ ፈርሶ ሁለቱ ጀርመኖች እንዲዋሃዱና አገራቸውም ከምዕራቡ ዓለም ጋር ለሽርካነት እንድትበቃ አድርገዋል።
የ 'ግላስኖስት' ነፃ ንግግር ፖሊሲያቸውም ቀደም ሲል አይደፈሬ የነበረውን ይሶቭዬት መንግሥትና ኮሙኒስት ፓርቲን ለመተቸት አስችሏል፤ እንዲሁም በቦልቲክ ሪፐብሊኮች ላቲቪያ፣ ሊቱዋኒያ፣ ኢስቶኒያና በሌሎችም ግዛቶች የንገንጠል ጥይቄን ለመቀስቀስ አስችሏል።
Mikhail Gorbachev signed a landmark treaty to eliminate intermediate-range missiles with the then US president Ronald Reagan. Credit: AP / Bob Daugherty ጎርቫቾቭ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋርከ ታሪካዊው የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ቅነሳ ስምምነት ላይ በመድረስና የበርሊን ግንብ ሲፈርስም የሶቪዬትት ጦር እርምጃ እንዳይወስድ ማድረ በማስቻላቸው በ1990 ከፕሬዚደንት ሬገን ጋር የሰላም ኖቤል ሽልማት ተቀብለዋል።