የጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ሌበር ፓርቲ ራሱን ችሎ መንግሥት ማቆም የሚያስችሉት 76 የምክር ቤት ወንበሮችን አገኘ

*** አዲሱ 47ኛው የአውስትራሊያ ፓርላማ ጁላይ 26 / ሐምሌ 19 ይሰየማል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ የካቢኔ አባላቶቻቸውን ዛሬ ያስታውቃሉ።

News

Australian Prime Minister Anthony Albanese acknowledges fellow Labor colleagues during a Labor Party Caucus at Parliament House in Canberra, Tuesday, May 31. Source: AAP

የጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ሌበር ፓርቲ ራሱን ችሎ መንግሥት ማቆም የሚያስችሉት 76 የምክር ቤት ወንበሮችን አገኘ።

 

ለመጀመሪያ ጊዜ የታደመው የሌበር ፓርቲ ፌዴራል ምክር ቤት የግራና ቀኝ አንጃ ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኒዚ ወደ ስብሰባው አዳራሽ ሲገቡ ሞቅ ባለ ጭብጨባ ተቀብሏቸዋል።  

 

አቶ አልባኒዚ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ፓርቲያቸውን ከተቃዋሚነት ለመንግሥትነት ያበቁ አራተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው።

 

የሌበር መንግሥት ለማቆም የሚያስችለውን 76 የምክር ቤት ወንበሮች ድል አድርጎ ያገኘ ቢሆንም ጊልሞርን አሸንፎ 77ኛውን የምክር ቤት ወንበር ለማግኘት እየመራ ይገኛል። 

 

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ማክሰኞ ከቀትር በፊት ካንብራ ለታደሙት የሌበር ፌዴራል ምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግር ፓርቲያቸው እንደ መንግሥት አንድም በከንቱ የሚያጠፋው ቀን እንደማይኖር አመላክተዋል። 

News
Australian Prime Minister Anthony Albanese addresses fellow Labor colleagues during a Labor Party Caucus at Parliament House in Canberra, Tuesday, May 31, 2022. Source: AAP

አያይዘውም፤ መንግሥታቸው የሠራተኞችን ደኅንነት ለማስጠበቅ፣ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ፣ የአረጋውያን ክብካቤን ለማሻሻል፣ ማምረቻዎችን በስፋት አምራች ለማድረኛ የአየር ንብረት ለውጥ ጦርነት እንዲያከትም የሚያደርግ መሆኑን አስታውቀዋል። 

 

የነባር ዜጎች የፓርላማ ድምፅና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መቋቋም በዚህ ዓመት ውስጥ ዕውን እንደሚሆን ገልጠዋል።

 

47ኛው የአውስትራሊያ ፓርላማም ጁላይ 26 / ሐምሌ 19 እንደሚከፈት ተናግረዋል።

 


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now