ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ የአዲሱ መንግሥት ሚኒስትሮቻቸውን ይፋ አደረጉ

*** የመጀመሪያዋን የፌዴራል ሴት ሙስሊም ሚኒስትር አን አሊን ጨምሮ 13 ሴቶች በአዲሱ ሌበር መንግሥት በሚኒስትርነት ማዕረግ ተመድበዋል፤ 19 ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነቶች ተሰጥቷቸዋል።

News

Australian Prime Minister Anthony Albanese. Source: AAP

ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ አዲሱን የካቢኔና ከካቢኔ ውጭ ያሉ ሚኒስትሮቻቸውን የሥራ ምደባ ይፋ አደረጉ።

የሌበር ፓርቲ የጊልሞር ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ወንበር በማሸንፍ በጠቅላላው 77 የምክር ቤት ወንበሮችን በመያዝ ራሱን ችሎ መንግሥት ለማቆም በቅቷል። 

የመጀመሪያዋን የፌዴራል ሴት ሙስሊም ሚኒስትር አን አሊን ጨምሮ 13 ሴቶች በአዲሱ ሌበር መንግሥት በሚኒስትርነት ማዕረግ ተመድበዋል (10ሩ የካቢኔ አባላት ናቸው)፤ ጠጨማሪ 19 ሴቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነቶች ተሰጥቷቸዋል። 

News
Anne Aly, Incoming Minister for Early Childhood Education, and Minister for Youth. Source: Getty

የሴት ካቢኔ አባላቱ፤

  1. ሴናተር ፔኒ ዎንግ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
  2. ሴናተር ካቲ ጋለኸር - የፋይናንስ ሚኒስትር - የሕዝብ አገልግሎት ሚኒስትር -  የሴቶች ሚኒስትር
  3. ታኒያ ፒልበርስክ - የአካባቢና ውኃ ሚኒስትር
  4. ካትሪን ኪንግ - የመሠረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ የሪጂናል ልማትና የአካባቢ መንግሥት ሚኒስትር
  5. ሊንዳ በርኒ - የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሚኒስትር
  6. አማንዳ ሪሽዎርዝ - የማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር
  7. ጁሊ ኮለነስ - የቤቶች ሚኒስትር የቤት አልባነት ሚኒስትር የአነሰተኛ ንግድ ሚኒስትር
  8.  ሚሼል ሮውላንድ - የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር
  9. ማድሊን ኪንግ - የሃብቶች ሚኒስትር - የሰሜናዊ አውስትራሊያ ሚኒስትር 
  10. ክሌየር ኦኒል - የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር - የሳይበር ደኅንነት ሚኒስትር ናቸው። 

አቶ አልባኒዚ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሪቻርድ ማርልስን የመከላከያ ሚኒስትር፣ ቶኒ በርክ የሠራተኛና መሥሪያ ቤቶች ግንኙነት ሚኒስትርና የሥነ ጥበብ ሚኒስትር፣ ማርክ በትለር የጤናና አረጋውያን ክብካቤ ሚኒስትር፣ ክሪስ ባወን የአየር ንብረት ለውጥና ኃይል ሚኒስትር፣ ቢል ሾርተን የብሔራዊ ግብረ አካል ጉዳተኞች ኢንሹራንስ ዕቅድ ሚኒስትርና የመነግሥት አገልግሎቶች ሚኒስትር፣ ማርክ ድሪፈዝ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ብሬንደን ኦከነር የክህሎቶችና ስልጠና ሚኒስትር፣ ጄሰን ክሌየር የትምህርት ሚኒስትር፣ ማሪ ዋት የግብርና ሚኒስትር የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር፣ ኢድ ሁሲክ የኢንዱስትሪና ሳይንስ ሚኒስትር፣ አንድሩ ጂለስ የኢሚግሬሽን፣ ዜኘትና መድብለባሕል ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል።   

 

በተጨማሪም ከካቢኔ ውጭ ያሉ ሚኒስትራትንና ሚኒስትር ደኤታዎችን ሹመቶችን ሰጥተዋል። 

 

ተሿሚ ሚኒስትሮች ነገ ቃለ መሃላ በመፈፀም ወደ የሥራ ኃላፊነቶቻቸው ይሰማራሉ።

 

በዘንድሮው አገራዊ ምርጫ ድል ተነስቶ ለተቃዋሚነት የተዳረገው የሊብራል / ናሽናልስ ጥምር ቡድንም በበኩሉ የሥራ መደብ ክፍሎችን በነገው ዕለት ያስታውቃል ተብሎ ይጠበቃል። 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now