SKIP TO MAIN CONTENT

ወላይታ ዞን አዲስ አስተዳዳሪ ሾመ

*** የወላይታ ዞን ምክር ቤት

Wolayta
Dr Endrias Geta Source: Supplied

1 min read

Published

By Demeke Kebede


Skip to article content

የወላይታ ዞን ምክር ቤት  ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ዶክተር እንድሪያስ ጌታን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ መሾሙን አልዓይን ዘግቧል፡፡

የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር እንድሪያስ በዞንና በክልል ደረጃ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች መስራታቸው በሹመቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ 

የቀድሞው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኮምቤ “ከብልጽግና ፓርቲ ሥነ ምግባር በወጣ መንገድ  ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በማለት ለውጡን ለመቀልበስ በውስጥና በውጭ ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ እንዳለ ደርሼበታለሁ” በማለት የፓርቲው የደቡብ ቅርንጫፍ አቶ ዳጋቶን ሰሞኑን ከኃላፊት ማንሳቱ ይታወሳል፡፡


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now