የቡድን 7 መሪዎች ከቻይና ጋር ስትራቴጂካዊ ፉክክር ውስጥ ገቡ

*** የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በወርኃ ጁን መጨረሻ ወደ ሥራ ሊመለሱ ነው

G7 summit

Source: AFP via Getty Images

የቡድን ሰባት መሪዎች ለደሃ አገራት "በዕሴት የሚመራ፣ የላቀ ጥራት ደረጃ ያለውና ግልፅነትን የተላበሰ" መሠረተ ልማት በሚል ዕሳቤ ከቻይና ሉላዊ የሐር መንገድ ፕሮጄክት ጋር ፉክክር ለማድረግ ወስነዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ አነሳሽነት የተነደፈው "የተሻለ ዓለም መልሶ መገንባት" ፕሮጄክት "ከቻይና ጋር ስትራቴጂያዊ ፉክክር" ለማድረግ የታሰበ ሲሆን ከቻይና ተፅዕኖ ጋር ለመቀናቀን የትኩረት ዒላማውን ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የላቲን አሜሪካና አውሮፓ አገራት አድርጓል።  

በቡድን 7 ስብሰባ ላይ በተሳታፊነት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አውስትራሊያ የኢንዶ - ፓስፊክ አካባቢን በማርጋቱ ረገድ ድጋፎቿን እየቸረች እንደሆነ ገልጠዋል።

ሞሪሰን - ባይደን

 

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ጋር በአገረ እንግሊዝ እየተካሔደ ባለው የቡድን ሰባት አገራት ጉባዔ ላይ የጎንዮሽ ስብሰባ በማድረግ ተገናኝተዋል።

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም በዚሁ 40 ደቂቃዎች በፈጀ ስብሰባ ላይ ታድመዋል።

G7 summit
Scott Morrison met with US President Joe Biden and UK Prime Minister Boris Johnson during the G7 summit in Cornwall on Saturday, 12 June. Source: The prime minister's office

አቶ ሞሪሰን ስብሰባውን አስመልክተው ሲናገሩ "ዓለማዊ አተያያቸውን የሚጋሩ የወዳጆችና ሽርካዎች ስብሰባ" በማለት የገለጡት ሲሆን፤ አክለውም ከመሪዎቹ ጋር መታደም መቻላቸውም ትልቅ ዕድል እነደነበረ ተናግረዋል። 

አውስትራሊያ የቡድን 7 አባል ባለመሆኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሪሰን በስብሰባው ላይ የተገኙት በአስተናጋጇ አገር ጠቅላይ ሚኒስትር  ጆንሰን በተደረገላቸው ግብዣ ነው።

 

 የቪክቶሪያ ፕሪሚየር

በአከርካሪ ጉዳት ሳቢያ ከወርኃ ማርች ጀምሮ በሕክምና ላይ የነበሩት የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በዚህ ወር መጨረሻ ጁን 28 ወደ ሥራ ገበታቸው ይመለሳሉ።

አቶ አንድሩስ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት በሜልበርን አልፍሬድ ሆስፒታል ነው። አቶ አንድሩስ የዕረፍት ጊዜያቸውን ለማሳለፍ አርፈውበት ከነበረው ቤት ደረጃዎች ላይ በውደቅ ሲሆን፤ በርካታ ጎድኖቻቸው የመሰበር አደጋ ደርሶባቸዋል።

Victorian Premier Daniel Andrews.
Victorian Premier Daniel Andrews. Source: AAP

የ48 ዓመቱ ፕሪሚየር የሕክምና ግልጋሎት ላበረከቱላቸው ባለሙያዎች፣ ለቤተሰባዊ ድጋፍ ባለቤታቸውንና ልጆቻቸውን፤ እንዲሁም በተጠባባቂ ፕሪሚየርነት አመራሩን ተረክበው ቪክቶሪያን ላስተዳደሩት ጄምስ ሜሊኖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።  

 

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now