ኖቫክ ጆኮቪች ኒክ ኪሪዮስን በማሸነፍ ለአራተኛ ጊዜ የዊምበልደን አሸናፊ ሆነ።
ውድድርሩ ለአራት ዙር የተከናወነ ሲሆን ውጤቱ ((4-6 6-3 6-4 7-6 (3) )) ሆኖ ተጠናቋል።
ጆኮቪች በዊምበልደን ሲያሸንፍ ይህ ለሰባተኛ ጊዜ ሲሆን በአጠቃላይም ታላላቅ የቴኒስ ውድድሮችን በአንደኛነት ሲያጠናቅቅ ለ21 ጊዜ ሆኗል ።
ሌይተን ሂወት በ2002 የዊምበልደ አሸናፊ ከሆነ በኋላ ለአውስትራሊያ በወንዶች ቴኒስ የዊምበልደን ተስፋን ያቆጠቆጠው የትናንቱን የኖቫክ ጆኮቪች እና ኒክ ኪሪዮስን ጨዋታ ነበር።
የ27 አመቱ ኪሪዮስ በበኩሉ ለዊምበልደን የመጨረሻ የዋንጫ ውድድር ላይ እደርሳለሁ ብሎ አስቦ እንደማይውቅ የተናገረ፤ ሲሆን በውጤቱም ለጆኮቪች የእንኳን ደስ ያለህ መለክትን አስተላልፏል ። ኖቫክ ጆኮቪች በበኩሉ ለኪሪዮስ ያለውን ከበሬታ እና ድንቅ ችሎታውን አድንቋል ።