አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ዲዬጎ ማራዶና በ60 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

*** የዝነኛው እግር ኳስ ኮከብ ማራዶና በልብ ድካም ለሕልፈተ ሕይወት መዳረግ በዓለም እግር ኳስ ቤተሰብ ዘንድ ብርቱ ኃዘንን አሳድሯል

Maradona

Con la maglia dell'Argentina, Diego Amando Maradona ha segnato 34 gol in 91 partite, conquistando il Mondiale del 1986 in Messico. Source: AAP Image/AP Photo/Carlo Fumagalli

ዲዬጎ ማራዶና በዓለም የእግር ኳስ ታሪክ ከሕይወት በላይ ግዘፍ ነስቶ በስፖርቱ ዓለም አንጸባራቂ አሻራውን ትቶ በ60 ዓመቱ ያለፈው ረቡዕ ዕለት ከቦነስ አይረስ ከተማ ፈንጠር ብሎ ባለው ቤቱ በልብ ድካም ሕመም ነው።  

ማራዶና በቅርቡ በነበሩበት የጤና ችግሮች ሳቢያ አስቸኳይ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ ግድ ተሰኝቶ ነበር። 

የአርጀንቲና ፕሬዚደንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ ታላቅ የእግር ኳስ ኮከብ የነበረውን ማራዶናን ክብር ለመቸር የሶስት ቀናት ብሔራዊ የኃዘን ቀን አውጀዋል።

የአርጀንቲና እግር ኳስ ማኅበርም በበኩሉ የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ገልጦ "ዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ሁሌም ልባችን ውስጥ ትኖራለህ" ሲል ልባዊ ከበሬታና ፍቅሩን ገልጧል።

ማራዶና የትውልድ አገሩን አርጀንቲና ለ1986ቱ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ድል አብቅቷል።

እንዲሁም በ1990 የአርጀንቲና ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ጣሊያን ላይ ለፍጻሜ ግጥሚያ አድርሷል በ2010ሩ የደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫም የመሪነት ሚና ተጫውቷል።

ብራዚሊያዊው ታላቁ የእግር ኳስ ኮከብ ፔሌም "እኔ ውድ ጓደኛዬን፤ ዓለም እጅግ ዝነኛ ሰውን አጥቷል" ሲል ኃዘኑን ገልጧል። 

ፕሬዚደንት ፈርናንዴዝም በበኩላቸው " ከዓለም ታላቅ ከፍታ ላይ አድርሰኸናል፤ በእጅጉም ደስተኞች አድርገኸናል"

"አንተ የታላላቆች ሁሉ ታላቅ ነበርክ። ከእኛ ጋር በመሆንህ እናመሰግንሃልን። በሕይወት ዘመናችን ሁሉ በናፍቆት እናስብሃለን" ሲሉ፤

ናፖሊ "ዲዬጎ - ለዘላለሙ ቻዎ!" ብሏል።

 


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now