የባርቤዶስ ሪፐብሊክ ምሥረታ ለአውስትራሊያ ሪፐብሊካን ንቅናቄ አራማጆች አጀንዳ ሆኗል

*** የላሊበላ ከተማና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመንግሥት ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጠ

Homeland Report

Queen Elizabeth II receives then-Governor General of Barbados Dame Sandra Mason during a private audience at Buckingham Palace in 2018. Source: AAP

በዚህ ሳምንት ውስጥ ከቅኝ ግዛት ታርኳ ተላቅቃ የዓለም አዲሲቱ ሪፐብሊክ ለመሆን የበቃቸው ባርቤዶስ አውስትራሊያ ውስጥ የሪፕበሊክ ጉዳይ ዳግም የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ እንዲነሳ አድርጓል።

የባርቤዶስ ሪፐብሊክ ምሥረታ አውስትራሊያን ጨምሮ በመላው ዓለም በእንግሊዝ ሕገ መንግሥታዊ  የዘውድ ፓርላማ አስተዳደር ስር ባሉ አገራት ዘንድ ቀልብ ስቦ መነጋገሪያ ለመሆን በቅቷል።  

የብሔራዊ አውስትራሊያ ሪፕብሊክ ንቅናቄ ዳይሬክተር ሳንዲ ቢያር የባርቤዶስን እርማጃ የሚያደንቁና በምሳሌነትም የሚመለከቱት መሆኑን ገልጠዋል። 

አያይዘውም “አውስትራሊያ በተመሳሳይ መልኩ በተቻለ ፍጥነት ሪፐብሊክ ስትሆን ማየት እንሻለን። ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ዙፋን ላይ እያሉ ሪፑብሊክ መሆንን እንወዳልን። ለግልጋሎታቸውም በሕይወት ሳሉ ሙሉ ነፃ አገር በማቆም ማምስገን እንሻለን" ብለዋል። 

ላሊበላ

የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሺያ እና ፋኖ የላሊበላ ከተማን እና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠራቸውን የመንግስት የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ምሽቱን አስታውቋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎቱ እንዳለው ጥምር ሃይሎቹ የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር በግስጋሴ ላይ ይገኛሉ ሲልም ገልጿል።

ሚኒስትሩ ዶር ለገሰ ቱሉ ረቡዕ ረፋድ ላይ በሰጡት መግለጫ የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ በጋሸና ግንባር በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠሩን አስታውቀው ነበር።

 በሕወሓት በኩል እስካሁን የመንግሥትን መግለጫ አስመልክቶ ይፋ መግለጫ አልወጣም።


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now