SKIP TO MAIN CONTENT

የዓለም የሴቶች ቴኒስ ኮከቧ አሽ ባቲ በ25 ዓመቷ የቴኒስ ዓለም በቃኝ አለች

*** "የዛሬዋ ቀን ለእኔ በጣሙን አዋኪ ናት። ከቴኒስ መሰናበቴን ስገልፅ በሲቃ ተመልቼ ነው" አሽ ባቲ

News
Ash Barty has announced her retirement from tennis. Source: AP

1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

በሴቶች ቴኒስ ከዓለም የአንደኛ ደረጃ ሠንጠረዥ ላይ ያለችዋ አውስትራሊያዊት አሽ ባቲ በ25 ዓመቷ ከቴኒስ ለመጠወር መወሰኗን ዛሬ ረቡዕ ማርች 23 በኢንስታግራም ገጿ አስተወቀች።

አሽ በወርኃ ጃኑዋሪ መጨረሻ ግድም በሜልበርን በተካሔደው የአውስትራሊያ ኦፕን ሻምፒዮን ከሆነች ገና ድፍን ሁለት ወራት እንኳ አልሞላትም።

ከቅርብ ጓደኛዋና የቀድሞ ቴኒስ ኮከብ ከነበረችው ካሲ ዴላክዋ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ከቴኒሱ ዓለም ከነአካቴው ለመለየት መወሰኗን ስትናገር "የዛሬዋ ቀን ለእኔ በጣሙን አዋኪ ናት። ከቴኒስ መሰናበቴን ስገልፅ በሲቃ ተመልቼ ነው" ብላለች። 

ስፖርቱ ክብርና ስኬት የተመላበት ሕይወትን እንደቸራት ገልጣም፤ በስፖርቱ ዓለም ጉዞዋ ድጋፋቸውን ለቸሯት ሁሉ ምስጋናዋን አቅርባለች።  


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now