SKIP TO MAIN CONTENT

በእነ ጃዋር መሐመድ ላይ አስር ተደራራቢ የክስ መዝገብ መዘጋጀቱን ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ

*** ክሱ ለተከሳሾቹ መስከረም 11 ቀን 2013 እንደሚደርስ ተገልጧል

AG
Source: AG

1 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ጃዋር መሐመድ ፤ አቶ በቀለ ገርባ ፤ አቶ ሀምዛ አድናን እንዲሁም በሌሉበት የተከሰሱትን  የኦሮሚያ ሜዲያ ኔትወርክ (OMN) ደጀኔ ጉተማ ፤ ዶ/ር ብርሃነመስቀል አበበ እና ፀጋዬ ረጋሳን ጨምሮ በአጣቃላይ በ24 ሰዎች ላይ ክስ መክፈቱን ገለጠ።

የክሱ ጭብጥም ተከሳሾች እንደየተሳትፏቸው፤

  • በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ
  • የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 በመተላለፍ
  • የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 761/2004 በመተላለፍ
  • የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በመተላለፍ በፈፀሙት ወንጀል መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 260215 አስር ተደራራቢ ክሶችን መክፈቱን ገልጿል።

 ተከሳሾቹ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ይደርሳቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now