አውስትራሊያ ከ29 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚ ድቀት እንዳጋጠማት ይፋ አደረገች _ ይህ ለእርስዎ ምን ማለት ነው

አውስትራሊያ ከ29 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ የገባች ሲሆን ፤ ከባለፈው ጁን ወር ጀምሮ የነበረው የሶስት ወር የመረጃ ውጤትም ያሳየው የአገር ውስጥ ምርት እድገት በሰባት በመቶ ዝቅ ማለቱን ነው ፡፡

Australia's economy has suffered its sharpest quarterly drop since the Great Depression.

Australia's economy has suffered its sharpest quarterly drop since the Great Depression. Source: AP

አውስትራሊያ ከ29 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚ ድቀት እንዳጋጠማት ይፋ አደረገች _ ይህ ለእርስዎ ምን ማለት ነው

አውስትራሊያ ከ29 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ የገባች ሲሆን ፤ ከባለፈው ጁን ወር ጀምሮ የነበረው የሶስት ወር የመረጃ ውጤትም ያሳየው የአገር ውስጥ ምርት እድገት በሰባት በመቶ ዝቅ ማለቱን ነው ፡፡

የመጀመሪያው የኢኮኖሚ እድገት ማሽቆልቆል የታየው ባለፈው ማርች ወር ሲሆን ይህውም 0.3 በመቶ ነበር ፡፡ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሁለተኛው ዙር ማእበል ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ደረጃ እንደጎዳውም የቅርብ ጊዜው ውጤት አመላክቷል ፡፡

“ እንደ አገር ላለፉት 28 አመታት በተከታታይ ያሳየነው የኢኮኖሚ እድገት በይፋ አብቅቷል ሲሉም ጆሽ ፍራይድንብርግ ተናግረዋ ፡፡”

አውስትራሊያ ከሌሎች የአለማችን አገሮች ጋር ስትነጻጸር በምን ያህል ርቀት ላይ ትገኛለች ?

ምንም እንኳን የአውስትራሊያ ኢኮኖሚ እድገት ማሽቆልቆል ጅምሯል ቢባልም ከሌሎች ያደጉ አገራት ጋር ሲነጻጸር አሁንም ቢሆን አውስትራሊያ ያለችበት ደርጃ በእጅጉ የተሻለ የሚባል ነው ፡፡

በኮሮና ሳቢያ ባለፈው ጁን ወር አገሪቱን ሙሉ ለሙሉ ዝግ ያደረገቸው እንግሊዝ ያሳየቸው የኢኮኖሚ ድቀት 20. 4 በመቶ ሲሆን ውጤቱም አገሪቱን በአለማቸን ካሉት ታላላቅ አኮኖሚዎች ሁሉ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት እንዳጋጠማት አረጋግጧል፡፡

የአገር ውስጥ ምርት እድገት በአሜሪካ 9 በመቶ ያሽቆለቆል ሲሆን ጀርመን እና ካናዳም ተመሳሳይ ውጤትን አስመዝግበዋል ፡፡

ስኮት ሆስለም በሲድኒ ክሬስቶን ዌልዝ ማኔጅመንት የኢንቨስትመንት ዋና ሃላፊ ለ ኤስ ቤ ኤስ እንደተናገሩት አውስትራሊያ አሁን ባለችበት ደርጃ እንድትቀመጥ ያደርጋት ከወረርሽኙ በፊት የነበራት ጠንካራ የገንዘብ ጥሪት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ የመጨረሻውን የኢኮኖሚ ድቀትን ያስተናገድነው ከ30 አመታት በፊት ነው ይህ  በግልጽ የሚያሳየን ያልተቋረጠ እድገትን ስናስመዘግብ መቆየታችንን እና ውጤቱም የገንዘብ አቅማችንም በጥሩ ሁኔታ ማቀመጡን ነው ፡፡ ”  ብለዋል

አያይዘውም “ ከሌሎች አገሮች በተሻለ ሁኔታም ለዜጎች የገንዘብ ድጎማን ለማድረግ ችለናል ፤ መዘጋት የሚገባቸውንም የንግድ ተቋማት በቶሎ መዝጋታችን አውስትራሊያ በኮቪድ19 ወቅት የተሻላ ጊዜ እንዲኖራት አድርጓል ፡፡

ማስወገድ የሚቻል ነበርን ?

በካንብራ ዩኒቭርሲቲ በፖለቲካ አኮኖሚ እና ማህበረሰብ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ጆን ሃውኪንስ እንደሚሉት ከሆነ መንግስት አሁን ያለውን የኢኮኖሚ ድቀት እንዳይከሰት ለማድረግ ከወሰድው እርምጃዎች ውጭ ሌላ ይኖራል ብዬ አላስብም ፡፡

“ ለማስወገድ የሚያስችል ምንም መንገድ የለም ፤ ከማርች ጀምሮ የነበረውን የሶስት ወር ውጤት ለማስተካከል መሰራት የነበረበት እና ሳይሰራ የቀረ ምንም ነገር አልነበረም ፤ መንግስት ትልቅ የሚባል የገንዘብ ድጋፍን አድርጓል ከጊዜ አንጻር ስናየው ምናልባትም ትንሽ ቀደም ሊያደርገው ይችል ነበር ፤ ነገር ገን በምንም መልኩ የማናስወግደው ነበር ፡፡  ” ሲሉ ተናግረዋል

አያይዘውም “ ምናልባትም ማርች ላይ ተዘግተው የነበሩት የንግድ ተቋማት ባይዘጉ ኖሮ በጥቂቱ የተሻለ ውጤትን ማሳየት ይቻል ነበር ልንል እንችል ይሆናል ፤ በተቃራኒው በረካታ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ከጁን እስከ ሴፕቴምበር ያለውን ውጤት እጅግ አስከፊ ሊያደርገው ይችልም ነበር ፡፡ ”

የኢኮኖሚ ድቀቱ ለእርስዎ ምን ማለት ነው ?

እንደ ተባባሪ ፕሮፌሰር ሃውኪንስ ከሆነ  የኢኮኖሚ ድቀት የሚታየው “ የእርስዎ ጎረቤት ስራቸውን ሲያጡ ነው ፡፡ ” እርስዎ ስራዎትን በሚያጡ ጊዜ  በቀጥታ የኢኮኖሚው ድቀት በርስዎ ላይተጸኖ ማሳረፉን ይጀምራል  ፡፡

“ አንዳንድ ሰዎች የተወሰነውን የስራ ሰአታቸውን ሊያጡ ይችላሉ  ፤ ያም የሌሎችን ህይወት በተለያያ ሁኔታ ሊነካ ይችላል ፡፡ ለምሳሌ የደሞዝ ጭማሪ ለማግኘት ረጅም ጊዜ መጠበቅን ሊጠይቅ ይችላል ፡፡ ”

ለምን ያህል ጊዜ ሊቆይ ይችላል ?

እንደ አቶ ሆስለም አባባል ከሆነ በአሁኑ ጊዜ የታየው የኢኮኖሚ ድቀት ባልተለመደ እና ልዩ በሆነ ምክንያት ማለትም  የህብረተሰብን ጤናን አደጋ ውስጥ ላለማስገባት ሲባል የንግድ ተቋማትን በመዝጋት የተከሰተ ስለሆን ከዚህ ቀድሞ ከታዩት ጋር ሲነጻጸር ብዙ የሚቆይ አይሆንም ፡፡

“ ይህ በ 1991 እንዳስተናገድነው አይነት ያለ የኢኮኖሚ ድቀት አይደለም ፤ ወይም አለማችንን በ2008 እና 2009 እንደፈተነው አይነትም አይደለም ፤ ይህንን በቀላሉ ልንገልጸው የምንችለው የንግድ ተቋማትን በመዝጋት ሳቢይ የተከሰት ነው ፡፡ ስለሆነም በአሁን ሰአትአንዳንድ ተቋማት በመከፈታቸው ሳቢያ አኮኖሚው ላይ መሻሻልን ማየት የጀመርን ሲሆን ህብረተሰቡም ገንዘቡን ማውጣት ጀምሯል ፡፡ ”

“ ጥልቀቱን ስንመለከት ከዚህ ቀደም ካየናቸው ሁሉ የበለጠ ሲሆን ፤ ቆይታውን ስንመለከት ግን በእኔ ግምት መሰረት ከግማሽ አመት በላይ እንደማይቆይ እና ካሳለፍናቸው የኢኮኖሚ ግሽበት ጊዜያት ሁሉ ይህኛው ፈጣን እንደሚሆን ነው ፡፡”

አቶ ሃውኪንስ እንደሚሉት ከሆነ የገቢ ምንጫቸውን በቱሪዝም እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ ያደረጉቱ ፤ አኮኖሚያቸው መቼ ሊያገገም ይችላል የሚለውን ለመወሰን ፤ ሌሎች አገራት ቫይረሱን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ጥረት መጠን እና የተቀመጡት የድንበር ክልከላዎች የሚከፈቱበት ጊዜያት የሚወስነው ይሆናል ፡፡

በአውስትራሊያ የሚኖሩ ዜጎች 1. 5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ አለባቸው፡፡ መሰባሰብን በተመለከተም የክልሉን ገደብ መመልከት ያስፈልጋል፡፡የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በአሁን ሰአት በሰፊው ይደረጋል፡፡የብርድ ወይም ጉንፋን ምልክቶችን ካሳዮ ሃኪምዎ ጋር በመደወል ምርመራን እንዲያደርጉ መጠየቅ የሚችሉ  ሲሆን ወይም coronavirus Health Information Hotline on 1800 020 080 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

The federal Government’s coronavirus tracing app COVIDSafe በይፋ ስለወጣ በስልክዎ ላይ ይጫኑ፡

ኤስ ቢ ኤስ ለአውስትራሊያውያን መድብለ ባህል ማህበረሰብ አዳዲስ ኮቪድ- 19 መረጃዎችን በትጋት ያደርሳል፡፡ ዜናዎች እና መረጃዎች በ63 ቋንቋዎች ይገኛሉ ከwww.sbs.com.au/coronavirus 

   


Share

4 min read

Published

Presented by Martha Tsegaw


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service