በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸውን የሚለይ አፕ አውስትራሊያ ይፋ አደረገች

COVIDSafe aplication

COVIDSafe aplication Source: PD

አውስትራሊያ የኮቪድሴፍ አፕ ይፋ አደረገች - አፑ በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸውን የሚለይ ነው ፡፡

 አፑ የተሰራበት አለማው ምንድን ነው ?

 አፑ በኮሮና ቫይረስ የተያዙትንና  ከነሱ ጋር ንከኪ ያላቸውን ሰዎች በቀላሉ ተከታትሎ ለማግኝት ይረዳል፡፡

ይህም የሚሆነው መረጃዎችን በስልክ ውስጥ በማስቀመጥ ለጤና ባለስልጣናት እንዲያገኙት በማድረግ ነው፡፡

መረጃው የሚቀዳውም አንድ ተጠቃሚ በአቅራብያ ከሚገኝ ከሌላ አፑን ተጠቃሚ  ሰው ጋር በ1.5 ሜትር ርቀት ከተገናኝ 15 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡

ኮቪድሴፍ አፕ COVIDSafe app ለመጫን ሙሉ ለሙሉ በግለሰቦች ፈቃደኝነት ላይ የሚመሰረት ሲሆን መንግስት በበኩሉ ሁሉም አውስትራሊያውያ ነዋሪዎች እንዲጭኑት ምክሩን ይለግሳል፡፡ ለምን ቢሉ ብዙ አውስትራሊያውያን በ COVIDSafe app በተገናኙ ቁጥር የቫይረሱን የስርጭት አቅጣጫ በቀላሉ ለመለየት ይረዳል፡፡

 ባለስልጣናቱ የኮቪድሴፍ መረጃ  እንዴት ይጠቀሙበታል?

 የኮቪድሴፍ አፕየተሰራበት ዋነኛ አላማው በአሁን ሰአት በስራ ላይ ያለውንና በ COVID-19 ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ መነካካት ያደረጉ ሰዎችን ተከታተሎ ለማግኘት የሚደረገውን የመረጃ አሰባሰብ ዘዴን ለመተካት ነው፡፡ ይህ አካሄድ  የቫይረሱን ስርጭት ሳይረዱ ለቤተሰብ ፤ ጓድኞች እና በማህበረሰቡ ውስጥ ለሚኖሩ ሌሎች ሰዎች እንዳያስተላለፉ ይረዳል፡፡

 የከተሞች እና ግዛቶች የጤና ባለስልጣናት መረጃዎችን የሚያገኙት በቫይረሱ የተያዘው ሰው በስልኩ ላይ ያለው መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ የጤና ባለስልጣናትም መረጃውን የሚጠቀሙበት ተለይተው መቀመጥ ወይም ምርመራ ሊያስፈልጋቸው የሚገባቸውን ሰዎች ለማሳሰብ ነው፡፡

የኮቪድሴፍ አፕቫይረሱ ከያዛቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት እና ንክኪ የነበራችውን ሰዎች ተከታትሎ የሚያገኝ ብቸኛው አፕ ሲሆን  በአውስትራሊያ መንግስትም ይሁንታን ያገኘ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ COVIDSafe app Health Department ድር ገዕ ይመልከቱ፡፡

 በ የኮቪድሴፍ አፕ ውስጥ የትኞቹን የግል መረጆዎች  ያጋራሉ ?

 ተጠቃሚዎች አፑን ሲጭኑ ስማቸውን፤ የስልክ ቁጥራቸውን ፤የፖስታ ሳጥን ቁጥራቸውንና እድሜያቸውን ይጠየቃሉ፡፡ከዚያም ሂደቱን ለማጠናቀቅ የኤስ ኤማ ኤስ መልእክት ይደርሳቸዋል፡፡

ኮቪድሴፍ ሌሎች  ኮቪድሴፍከተጫነባቸው ስልኮች ጋእ በብሉ ቱዝ አማካኝነት ግንኙነት ማድረግ ይችላል፡፡ ይህ አፕ ሌላ ተጠቃሚን መለየት ከቻለ ፤ ቀኑን ፤ሰአቱን፤ ርቀቱን ፤ የጊዜውን ርዝመት እና የመለያ ቁጥር ይመዘገባል፡፡ ይሁነና COVIDSafe app

ተጠቃሚው ያለበትን አቅጣጫ እንዲጠቁም አይጠበቅም፡፡

 የአፑ ተጥቃሚ በምርመራ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ምን ይከሰታል?

 በአፑ አማካኝነት የተሰበሰቡ ሌሎች የአፑን ተጠቃሚዎችን የማግኘት ሂደትን ያፋጥናል

ግለሰብችን ወላጆችን ወይም አሳዳጊዎችን በስልክ በማግኘት በቫይረሱ ምናልባት ተጋልጠው ሊሆኑ እንደሚቸሉ መንገር

የሚቀጥለው እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል ምክር መስጥት ለምሳሌ ፦

ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቸው ?

መቼ ፤ እንዴት እና የት ሄደው መመርመር እንደሚኖርባቸው?

ጓደኖችን እና ቤተሰቦችን እንዳይጋለጡ ምን ማደረግ እንዳለባቸው ?

የጤና ባለስልጣናት በቫይረሱ የተያዘውን ሰው ስም በምንም አይነት ይፋ አያደርጉም፡፡


Share

2 min read

Published

Updated

By SBS RADIO

Presented by Martha Tsegaw

Source: SBS Radio


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service