አውስትራሊያ መቀሌ ላይ የተሰነዘሩት የአየር ጥቃቶችና በሰሜን ኢትዮጵያ እየበረታ በመሔድ ያለው ግጭት አሳስቦኛል አለች

*** "አውስትራሊያ ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡና የአመፅ ድርጊትን እንዲያበቁ ጥሪ ታቀርባለች፤ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለአገሪቱ መረጋጋት ተቃርኖአቸውን በአስቸኳይ ገትተው መፍትሔን በድርድር እንዲሹ ታበረታታለች " የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜሪዝ ፓይን

News

Australia's Foreign Minister Marise Payne. Source: Getty

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜሪዝ ፓይን ዛሬ ኦክቶበር 20 ባወጡት መግለጫ በትግራይ መዲና መቀሌ ላይ የአየር ጥቃት መሰንዘራቸውን የሚያመለከቱ ሪፖርቶችና በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው ግጭት እየበረታ መሔድ አውስትራሊያን በብርቱ ያሳሰበ መሆኑን አስታወቁ። 

አያይዘውም፤ አውስትራሊያ እየተካሄደ ያለውን ግጭት፣ ወሲባዊ ጥቃት መፈጸምንና በረድኤት አቅርቦት ላይ ገጥመው ያሉ እጅግ ብርቱ ገደቦችን እንደምታወግዝና አንደኛ ዓመቱን ለማስቆጠር ተቃርቦ ያለው ግጭት በሰላማዊ ሰዎች ሕይወት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን አመላክተዋል። 

ሚኒስትሯ ለSBS አማርኛ በላኩት መግለጫቸው "አውስትራሊያ ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡና የአመፅ ድርጊትን እንዲያበቁ ጥሪ ታቀርባለች፤ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለአገሪቱ መረጋጋት ተቃርኖአቸውን በአስቸኳይ ገትተው መፍትሔን በድርድር እንዲሹ ታበረታታለች " ብለዋል። 

አክለውም፤ በርካታ አውስትራሊያውያን ከኢትዮጵያ ጋር የቅርብ ትስስሮሽ እንዳላቸው አመላክተው፤ በግጭቱ ሳቢያ ቤተሰባቸውና ወዳጆቻቸው ለተጎዱባቸው ጥልቅ ኃዘኔታቸውን ገልጠዋል። 

በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል አየር ኃይሉ የወሰደው እርምጃ የፈደራል መንግሥት ይዞታ በነበሩና ሕወሓት አገር ለማፍረስ እየተጠቀመባቸው በቆዩ ይዞታዎች ላይ መሆኑንና የኢፌዲሪ አየር ኃይል በፈጸመው ድብደባ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል ማለቱን መንግሥታዊ ምንጮች የገለጡ ሲሆን፤ ሕወሓት በበኩሉ በአየር ጥቃቱ ሁለት ሕፃናትን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አመላክቷል። 


1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now