SKIP TO MAIN CONTENT

የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት ቁጥር ወደ 7.4 አሻቀበ

በወርኃ ጁን 69,300 ሥራዎች ከስመዋል።

Unemployment rate in Australia falls further: SBS Sinhala News 12 March 2021
March unemployment rate will be announced this Thursday. Source: AAP

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከተጣሉት ገደቦች ጋር ተያይዞ የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት ቁጥር በወርኃ ጁን ውስጥ 7.4 ደርሷል።  

በዚሁ ጁን ወር ውስጥ  69,300 ሥራዎች ሲታጠፉ 210,800 ሰዎች ለቅጥር በቅተዋል።

የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ ዛሬ ሐሙስ ይፋ እንዳደረገው የግማሽ ቀን ሥራ በ 249,000 ከፍ ሲል፤ የሙሉ ቀን ሥራ በ 38,100 ዝቅ ብሏል። 

የሥራ አጥነት ቁጥር በወርኃ ኤፕሪል ከነበረበት 6.4 ፐርሰንት በወርኃ ሜይ ወደ 7.1 ከፍ ማለቱ የሚያመለከተው በማርች መጨረሻ ግድም የማኅበራዊ ርቀት መመሪያዎችን ለማስጠበቅ የተወሰዱት እርምጃዎች ተፅዕኖ እንደሆነም ተገልጧል።

የደቡብ አውስትራሊያ ሥራ አጥነት ቁጥር 8.8 ፐርሰንት፣ ምዕራብ አውስትራሊያ 8.7 ፐርሰንት፣ ኩዊንስላንድ 7.7 ፐርሰንት፣ የቪክቶሪያ ሥራጥነት ቁጥር 7.5 ፐርሰንት ላይ ሲረጋ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሥራ አጥነት ወደ 6.9 ወርዷል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now