ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፉት ደራሲ ሳልማን ሩሽዲ በስለት ተወጉ ደራሲው ጉበታቸው ተጎድቷል፤ አንድ ዓይናቸውንም ሊያጡ ይችላሉ 1 min read
Published 13 August 2022 2:24pm
Updated 13 August 2022 2:57pm
By NACA, Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS
Skip to article content Share this with family and friends
ሕንዳዊው - እንግሊዛዊ ደራሲ ሳልማን ሩሽዲ ኒውዮርክ ንግግር ለማድረግ በተጋበዙበት አዳራሽ መድረክ ላይ ሳሉ አንገትና ሆዳቸው ላይ ከ10 እስከ 15 ጊዜያት በስለት ተወግተዋል።
ወዲያውኑም ወደ ሆስፒታል በሂሊኮፕተር ተወስደዋል።
In this still image from a video, author Salman Rushdie is taken on a stretcher to a helicopter for transport to a hospital on Friday, 12 August 2022. Credit: AAP / AP ደራሲው በደረሰባቸው የስለት ውግ ሳቢያ ጉበታቸው የተጎዳ፣ አንድ ዓይናቸው ሊጠፋ እንደሚችልና መናገርም የተሳናቸው መሆኑን የደራሲው ወኪል አንድሩ ዋይሊ ተናግረዋል።
ሩሽዲ ሕክምና እየተከታተሉ ባሉበት ሆስፒታል የመተንፈሻ መሳሪያ የተገጠመላቸው መሆኑንም ተገልጧል።
ሳልማን ሩሽዲን በስለት የወጋው ተጠርጣሪ የ24 ዓመት ወጣት ሃዲ ማታር በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል። ሆኖም አደጋውን ለማድረስ ምን እንዳነሳሳው ፖሊስ ፍንጭ አልሰጠም።
Law enforcement officers detain a person outside the Chautauqua Institution, on Friday, 12 August 2022, in Chautauqua, New York. Credit: AAP / AP
የ75 ዓመቱ ደራሲ "The Satanic Verses" በሚለው የ1980ዎቹ መጽሐፋቸው ለዓለም አቀፍ ዝናና የሞት ዛቻ ዳርጓቸዋል።