SKIP TO MAIN CONTENT

8ኛው የዓመቱ በጎ ሰው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ተከናወነ

*** የኢፌዴሪ ርዕሰ ብሔር በክብር እንግድነት ተገኝተዋል

award
Source: Courtesy of PD

2 min read

Published

By Demeke Kebede


Skip to article content

የዘንድሮው የበጎ ሰው ልዩ ሽልማት በኢንተርንኮንቲኔንታል ሆቴል ተከናውኗል።

የኢፌዴሪ ርዕሰ ብሔር በክብር እንግድነት በመገኘት ለ8ኛ ጊዜ የተደረገውን የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች ሽልማት ሰጥተዋል።

 በዚህ መሰረትም

1) አቶ ካሊድ ናስር ፡

ባለፉት አምስት ወራት በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ምክንያት የገዛ መኖሪያ ግቢያቸውን ሳይቀር በመስጠት፣ መጠለያ የሌላቸውን በመደገፍ የበጎ አድራጎት ሥራ የሠሩ

2) አቶ ኪሮስ አስፋው ፡

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ያለማቋረጥ መቶ ጊዜ የሕዳሴ ግድብ ቦንድ የገዙ

3) ቢኒያም ከበደ ፡

የንባብ ለሕይወት መሥራች አዘጋጆች አንዱ እንዲሁም የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥን መስራች።

4) መሀመድ አልአሩሲ

የህዳሴው ግድብ ተሟጋች ፡ በተለይም በአረብኛ ቋንቋ ከግብፆች ጋር በሚዲያ እየተናነቀ የሚገኝ ወጣት

5) ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ፡

የአባይ ጉዳይ ተመራማሪውና የ"ዓባይ ዲፕሎማቱ" ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ

አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ መምህሩና ተመራማሪው እንዲሁም  በውሃ ዲፕሎማሲው ዘርፍ ከህዳሴ ግድቡ ግንባታ ጀምሮ አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚገኙት ፣ ብሎም መፅሃፍ የፃፉ

6) የሕክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ፡

የኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን ከተሰረተ ጀምሮ ራሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው የዜጎች ደኅንነት ለመጠበቅ ከፊት የተሰለፉ የጤና ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የ2012 የዓመቱ የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ  በመድረኩ የጤና ባለሞያዎችንና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በመወከል ተቀብለዋል።

7) ኢትዮ ቴሌኮም፡

በዓመቱ ውስጥ በተለይ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ በሰራቸው የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ የ2012 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ድርጅቱን በመወከል የተገኙት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ተቀብለዋል

8) በጉባ በሥራ ላይ የሚገኙ የህዳሴው ግድብ ሰራተኞች፡

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሰራተኞች፣ በቦታው ሆነው ጸጥታውን የሚቆጣጠሩ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፓሊስ አባላት የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ከመጋቢት 24/2004 ጀምሮ ሀገራችን የመጀመሪያ ዙር የውኃ ሙሌት እስካከናወነችበት ጊዜ እንዲሁም አሁንም ድረስ በጉባ በሥራ ላይ የሚገኙ የህዳሴው ግድብ ሰራተኞች የ2012 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በጉባ የሚገኙ ሁሉንም ሰራተኞች ወክለው ሽልማቱን የወሰዱት የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሆሮ ሲሆኑ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ሽልማቱን "ይህንን ፕሮጀክት እውን እንዲሆን በሚጥሩ  ሁሉ ስም እቀበላለሁ" ብለዋል፡፡

አክለውም "የምቀበለው  የሚቀጥለው አመት ግብ ከተሳካ ፕሮጀክቱ እንደተጠናቀቀ መውሰድ እንችላለን" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now