የመከላከያ ሠራዊት አክሱምንና አድዋን ተቆጣጠረ

*** ሠራዊቱ ወደ አዲግራት ከተማ እያመራ ነው

Axum and Adwa

A video released by the state-owned Ethiopian News Agency shows Ethiopian military sitting on an armoured personnel carrier next to a national flag Source: Ethiopian News Agency

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አክሱምንና አድዋን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም የአዲግራትን ዙሪያ መቆጣጠሩን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ በኅዳር 11- 2013 መግለጫው አስታወቀ፡፡

በመገለጭው ላይ እንደሠፈረው በምዕራብ ግንባር የሕወሓት ኃይልን እያጠቃ ያለው የመከላከያ ሠራዊት፣ ከሽሬ በኋላ ሰለህለሃ ላይ የመሸገ የሕወሓት ኃይል ገጥሞት እንደነበርና ሆኖም የተከላካይ ኃይሉን ሰብሮ በመግባት አክሱምን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገልጧል።

አያይዞም የመከላከያ ሠራዊቱ እንቲጮንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጥሮ ወደ አዲግራት ከተማ እያመራ እንደሚገኝ አመላክቷል።

በሕወሓት በኩል የአክሱምና አድዋ ከተሞችን መያዝ አስመልክቶ ለለጊዜው ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልተደመጠም።  


1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now