SKIP TO MAIN CONTENT

አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸውን ጨምሮ 4 የሕወሓት አመራሮች መደምሰሳቸው ተገለጠ

*** ዘጠኝ የአመራር አባላትም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

Sekoture Getachew
Sekoture Getachew Source: Sekoture Getachew

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Skip to article content

1.  ቃል አቀባይ ሴኮቱሬ ጌታቸው፣

2.  ዘርአይ አስገዶም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበረ፣

3.  አበበ ገብረመድህን የድምጸ ወያኔ ሃላፊ የነበረ፣

4.  ዳንኤል አሰፋ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበረ ከሹፌሮቻቸውና ከጥበቃዎቻቸው ጋር በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌዴራል የጸጥታ ተቋማትና በትግራይ ሕዝብና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተደረገ የተቀናጀ ዘመቻ መደምሰሳቸውን የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ተናግረዋል።

በተጨማሪም 9 ከፍተኛ አመራሮች፤

1.  ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ የቀድሞ የክልሉ አፈጉባኤ የነበረች፣

2.  ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣

3.  አቶ ተክለወይኒ አሰፋ የማረት ስራ አስፈጻሚ የነበረ፣

4.  አቶ ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣

5.  አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣

6.  አምባሳደር አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበረና የፖለቲካ ክንፉ የተቀላቀለ፣

7.  አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ሃላፊ የነበረ፣

8.  ወይዘሮ ምህረት ተክላይ የክልሉ ምክር ቤት ህግ አማካሪ የነበረች እንዲሁም

9.  አቶ ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ስራ ሂደት ሃላፊ የነበረ ሁሉም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

[ ኢዜአ ]

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now