"ልቤን ብትከፍቱት ኢትዮጵያዊ ነኝ” - ባምቢስ

*** የኢትዮጵያ ወዳጅ ባምቢስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Bambis

Charalambos N. Tsimas (AKA Bambis) Source: Rotary Addis

በአገሪቱ የመጀመሪያው ሱፐር ማርኬት እ.ኤ.አ. በ1931 የተከፈተው በአዲስ አበባ ፍትሕ ሚኒስቴር አካባቢ የተተከለው ሱፐር ማርኬት ነው፡፡

የዚህ ሱፐር ማርኬት መከፈት ለአካባቢው ባምቢስ የሚለውን መጠሪያም አጋብቶበታል፡፡ ባምቢስ የሱፐርማርኬቱ ይዞታም ቻራ ላምቦስ ሲማስ በተባሉ ግሪካዊ ባለሀብት ሥር ነበር፡፡

ግሪካዊው ሚስተር ባምቢስ ሲማስ ከአገራቸው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በ1944 ዓ.ም ነው። ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ገና የ21 ዓመት አፍላ ወጣት ነበሩ ፡፡

 ባምቢስ ሱፐር ማርኬትን ከከፈቱበት ጊዜ ጀምሮ  አካባቢው በስማቸው መጠራቱ ደስታ እንደሚሰጣቸውና እሳቸው ካለፉም በኋላ፣ ስማቸው ለዘላለም ኢትዮጵያ ውስጥ መቀጠሉን ሲያስቡት ኩራት እንደሚሰማቸው ተናግረው ነበር፡፡

ሚስተር ባምቢስ፤ ከሱፐር ማርኬት ስራቸው ጎን ለጎን ኢትዮጵዊያንን ለማገዝ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሰርተዋለወ። ‹‹ሞት በኩላሊት ይብቃ››ለተሰኘው የኩላሊት ህሙማን ማህበር የ1 ሚሊዮን ብር ‹በሮተሪ ክለብ በኩል ለግሰዋል፡፡ ሰበታ ውስጥ ለአይነ ስውራን ህክምና የሚያገለግል በ5 ሚሊዮን 120 አልጋዎች ያሉትና ባለ ሶስት ፎቅ ሆስፒታል አሰርተዋል፡፡

3 ትላልቅ አምቡላንሶችን ለሆስፒታል ለግሰዋል። ሁለቱን ለፖሊስ ሆስፒታል፣ አንዱን ደግሞ ለየካቲት ሆስፒታል አስረክበዋል፡፡ የኢትዮጵያው ወዳጅ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በትናንትናው ዕለት ነው።

 

 


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now