የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዛሬ ጁላይ 7 / ሰኔ 30 የአገር መሪነት ስልጣናቸውን የሚለቁ መሆኑን በይፋ አሳወቁ።
ይሁንና ፓርቲያቸው በምትካቸው አዲስ የፓርቲና የአገር መሪ እስከሚመርጥ ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ይቀጥላሉ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን አመራር በመቃወም 59 የመንግሥት ባለስልጣናት ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለቅቀዋል።
የተቃዋሚ ቡድኑ የሌበር ፓርቲ መሪ ኪይር ስታርመር የጆንስንን ስንብት "ማለፊያ ዜና" ያሉት ሲሆን፤ አክለውም፤ አቶ ጆንሰን የሚሰናበቱ ቢሆንም የሚያሻው "አግባብ ያለው የመንግሥት ለውጥ ነው" ብለዋል።