ፌዴራል በጀት 2020/21

*** አንኳር የበጀት መረጃ

جاش فرایدنبرگ خزانه دار استرالیا (راست) و اسکات موریسون نخست وزیر استرالیا

Source: AAP

ምጣኔ ሃብት

  • በ2020 የአውስትራሊያ ምጣኔ ሃብት በ3.75 ፐርሰንት ሲያሽቆለቁል በ2021 በ4.25 ያድጋል
  • ይፋ የሥራ አጥነት ቁጥር በዲሴምበር ወደ 8 ፐርሰንት ያሻቅባል፤ እስከ 2023 ስድስት ፐርሰንት ላይ ረግቶ እንደሚቆይ ይጠበቃል 

ዕዳና የተረፈ ፈሰስ ጉድለት

  • በ2021-22 የተረፈ ፈሰስ ጉድለት $213.7 ቢሊየን 
  • በ2021 -22 የተጣራ ዕዳ $703 ቢሊየን (ከጠቅላላ ምርት ዕድገት 36 ፐርሰንት) በጁን 2024 ወደ $966 ቢሊየን (ከጠቅላላ ምርት ዕድገት 44 ፐርሰንት) ከፍ ይላል

የታክስ ቅናሽ

  • ከ11 ሚሊየን በላይ ግብር ከፋይ አውስትራሊያውያን የኋላ ቀሪ ክፍያን አካትቶ ከጁላይ 1 ጀምሮ የታክስ ቅናሽ ያገኛሉ
  • ከ$50,000 - $90,000 በዓመት ገቢ ያላቸው በሳምንት እስከ $21 ቅናሽ ያገኛሉ
  • ከ$120,000 በሳምንት እስከ $49 ቅናሽ ያገኛሉ
  • በመንግሥት በኩል ግብር ከፋዮች ያገኙትን የታክስ ቅናሽ በሙሉ ለሸመታ በማዋል $12.5 ቢሊየን ለኢኮኖሚ ማዳበሪያ ያስገኛል ብሎ ያስባል

ሥራ

  • በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ 950,000 ሥራዎች ይፈጠራሉ ተብሎ ግምት ውስጥ ገብቷል

1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now