አውስትራያ ውስጥ የማኅበረሰብ ቴሊቪዥን ስርጭት ሰሞኑን ከነአካቴው ሊከስም ነው

በዚህ ወር መጨረሻ የማኅበረሰብ ቴሌቪዥን ስርጭት አውስትራሊያ ውስጥ ይከስማል። ይሁንና መንግሥት ስርጭቱ በኦንላይን እንዲቀጥል እያበረታታ ነው። ጣቢያዎቹ ግና በዚያ ሁነት መዝለቅ እንደማይችሉ ስጋታቸውን እየገለጡ ነው።

Community Television in Australia will soon cease broadcasting

C31's control room in Melbourne Source: SBS

የሜለበርን ቻናል 31 ከ 25 ዓመታት በላይ ስርጭቶቹን አየር ላይ አናኝቷል።

ሮቭ ማክማነስ፣ ሃሚሽ ብሌክና አንዲ ሊን የመሳሰሉ ዝነኛ አዝናኝ ባለሙያዎችን አፍርቷል።

ዋሊድ አሊ፣ ሱዛን ካርላንድና የአውስትራሊያ የመጀመሪያው የሙስሊም ቴሌቪዥን ትዕይንት 'ሳላም ካፌ' ኮከብ ናዚም ሁሴንንም ቀርጾ ለግዙፍ መድረክ አብቅቷል። 

ዝናን የተላበሰው የ 'ቫሲሊ የጓሮ እርሻ' ትዕይንት በግሪካዊ-አውስትራሊያዊው ቫሲሊ ካሁዲያዲስ ለታይታ ውልደት የበቃውም እዚያ ነው። 

የማኅበረሰብ ቴሌቪዥን የተቋቋመው ማናቸውም ፍላጎት ያላቸው ሰዎች፤ ምንም ዓይነት የሙያም ሆነ የመደብ ጀርባ ይኑራቸው ታሪካቸውን ወጥተው እንዲያጋሩበት ነው።

በቻናል 31 ታሪክ ውስጥም ጎልተው የሚታሰቡት እምብዛም የማይነሱ ማኅበረሰባትን ታሪኮች ለዕይታ ማብቃቱ ነው።

 ለቴሌቪዥን ጣቢያው ክስመት መነሻ በ2014 በወቅቱ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር የነበሩት ማልከም ተርንቡል የማኅበረሰብ ቴሌቪዥን ፈቃዶች እንዲሰረዙ በመወሰናቸው ነው።

እስከ ጁን 30 የጣቢያው ስርጭት ክስመት የዘገየው የተርንቡል ተተኪ የነበሩት ሚች ፋይፊልድ የማራዘሚያ ጊዜ ችሮታ ነው። 

ምንም እንኳ መንግሥት ጣቢያው ከአየር ወደ ኦንላይን ስርጭት እንዲሸጋገር ቢያበረታታም፤ የጣቢያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሼን ዳንሎፕ ግና መንግሥት ለሽግግር የሚሆን የገንዘብ ድጎማ በመንፈጉ ዘልቆ የመቀጠሉ ሁኔታ ፍርሃት ያሳደረባቸው መሆኑን ገልጠዋል።  

ቻናል 31 በጁን 30 ላይመለስ የአየር ላይ የስርጭቱ ሕይወቱ ለፍጻሜ ይበቃል።

 

 

 

 

 

 

 

 


1 min read

Published

By Naveen Razik

Presented by Kassahun Seboqa Negewo



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now