"ምዕራፍ ሁለት ተጠናቅቋል፤በሶሶተኛውና ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

*** የመከላከያ ሠራዊቱ ዕዳጋ ሐሙስን ተቆጣጥሯል

PM Abiy Ahmed

PM Abiy Ahmed Source: PMO Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በፌዴራል መንግሥቱና በሕወሓት መካከል የተፈጠረውን ጦርነት ሂደት አስመልክተው "በትግራይ ክልል የጀመርነው ሕግን የማስከበር እርምጃ ሁለተኛ ምዕራፍ ተጠናቅቋል። አሁን በመጨረሻውና በሶስተኛው ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን" ሲሉ ገልጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምዕራፎቹን ዓላማ ደረጃ በደረጃ ሲገልጡም፤

  • ምዕራፍ አንድ "በገዛ ወገኑ የተጠቃውን የመከላከያ ሠራዊታችንን አሰባስበንና አጠናክረን፣ ተቋርጦ የነበረውን የዕዝ ሰንሰለቱን ወደ ቦታው መልሰን ግዳጁን እንዲወጣ ማስቻል፣
  • ምዕራፍ ሁለት "የሕወሐትን ጁንታ ከየአካባቢው እያስለቀቀ፣ ዐቅሙንም ከጥቅም ውጭ እያደረገ፣ ሕዝቡን ከዚህ የክህደት ቡድን ይዞታ ነጻ በማድረግ፣ የመሸገበትን የመቀሌ ከተማ መክበብ ነበር። በዚህ መሠረት በዳንሻ፣ በሑመራ፣ በሽሬ፣ በሽራሮ፣ በአክሱም፣ በአድዋ፣ በአዲግራት፣ በአላማጣ፣ በጨርጨር በመሖኒ፣ በኮረምና በሌሎችም ቦታዎች በተወሰደ እርምጃ ሠራዊታችን ሕዝብ እየታደገና ድል እያደረገ ተጉዟል።
  • ምዕራፍ ሶስት "በመቀሌ የሚካሄደውና የክህደት ቡድኑን ለሕግ ለማቅረብ የሚደረግ የመጨረሻው እርምጃ ነው" ብለዋል።

አያይዘውም ለትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት እንዲሁም ለሕወሓት አመራር አባላት በ72 ሰዓታት ውስጥ "የሕዝብ ዕልቂት ከመፍጠርና ከተማ ከማውድውም ተቆጥባችሁ እጃችሁን በሰላም ለመስጠት ጊዜው አልፈረም" ሲሉ የጊዜ ገደብ ጥለዋል።

ይህ በእንዲህ አንዳለም የመከላከያ ሠራዊቱ በትናንትናው ዕለት "ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን መቆጣጠሩና በአድዋ ተምቤን መስመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጥያ መንገድ የገጠመውን ተዋጊ ኃይል ድል" ማድረጉንና መቀሌንም የመቆጣጠር እርምጃ ለመውሰድም ዙሪያውን ከብቦ እንዳለ የመከላከያ ሠራዊቱ ቃል አቀባይ አስታውቋል።

በሌላም በኩል የሕወሓት መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል "መቀሌን መክበብ የእነሱ ዕቅድ ነው፤ ይሁንና አልተቻላቸውም። በደቡብ ግንባር ለአንድ ሳምንት ያህል አንዲት ኢንች እንኳ ፈቀቅ ማለት አልቻሉም" ሲሉ ለሮይተርስ በቴክስት መልዕክት ገልጠዋል።

 


2 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now