የግላስጎ ኮፕ26 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በስምምነት ተጠናቀቀ

***ቪክቶሪያ ውስጥ በወንጀል ተጠያቂነት ዕድሜ ወደ 14 ከፍ እንዲል ተጠየቀ

COP26

COP26 President Alok Sharma (C) speaks during an informal plenary stocktake on day 14 of COP26 at SECC on November 13, 2021 in Glasgow, Scotland. Source: Getty

የተባበሩት መንግሥታት የግላስጎ አየር ንብረት ለውጥ ታዳሚዎች ዘንድ ለሁለት ሳምንታት አያሌ ሰዓታት ከፈጀ የአንድ - ለአንድ ድርድር በኋላ ከስምምነት ለይ ደርስዋል።

ከተወሰኑ ቅሬታዎችና ማመንታቶች በኋላም ቢሆን 197ቱም ታዳሚዎች ፊርማዎቻቸውን አኑረዋል።

የግላስጎ አየር ንብረት ለውጥ ትልም ሉላዊ ግለትን 1.5 ዲግሪ ሴልሲየስ ላይ መግታት ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ አየር ንብረት ለውጥ ተጠሪ ጆን ኬሪ የተደራዳሪዎቹን ከስምምነት ላይ ደርሶ ለፊርማ ፅድቅ መብቃትን በእጅጉ አድንቀዋል። 

የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተሳታፊ አገራት በሚቀጥለው ዓመት ኮፕ27 ዕቅዶቻቸውን አጠንክረው ይሁንታን ለመቸር ካይሮ ላይ ይገናኛሉ። 

የዘንድሮው ኮፕ26 ጉባኤ ደሃ አገራት የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እንዲችሉ ከ2025 ጀምሮ በዓመት የአንድ ትሪሊየን ዶላር ድጎማ እንዲያገኙ ተስማምቷል። 

 

ኮፕ26 የደንጊያ ከሰል                                              

በግላስጎ ጉባኤ ሕንድ፣ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ የደንጊያ ከሰልን ጨምሮ ሌሎች የቅሬተ አካል የኃይል ምንጮች ጠቀሜታ እንዲያከትም በስምምነቱ ረቂቅ ላይ መስፈሩን አንስተው ተቃውሞ አሰምተዋል። የሕንድ የአካባቢ ተፈጥሮና አየር ንብረት ሚኒስትር ቢሁበንደር ያዳቭ ረቂቅቁ ላይ "እንዲያከትም" በሚለው ቃል ፈንታ "እንዲቀንስ" በሚል እንዲተካ ሲሉ ጠይቀዋል።

አቶ ያዳቭ ሕንድ እጅጉን የደንጊያ ከሰል ጥገኛ መሆኗን አንስተው ተከራክረዋል። 

የሶስቱ አገራት ተቃውሞ በአውሮፓ ኅብረትና በርካታ የደሴት አገራት ቁጣን ያዘለ ተቃውሞ ደርሶበታል። ሆኖም ረቂቁ የደንጊያ ከሰል ምርት "እንዲቀንስ" በሚል ተተክቷል። 

የኮፕ26 ፕሬዚደንት አሎክ ሻርማ በጉባኤው ፍፃሜ ወቅት ሁሉም 197 ተሳታፊዎች ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሲያስታውቁ ዕንባቸው ፊታቸው ላይ ፈስሶ ነበር። 

 

ኮፕ26 አውስትራሊያ                                                      

 

የሉላዊ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ግላስጎ ላይ መጠናቀቅን ተከትሎ  ለፌዴራል መንግሥቱ ብርቱ ማሳሰቢያዎችና ትችቶች መድረስ ጀምረዋል።

የአየር ንብረት ምክር ቤት ዋና የምርምር ኃላፊ ሳይመን ብራድሾው አውስትራሊያ ግላስጎ ላይ የተገኘችው ባዶ እጇን እንደሆነና ለፓስፊክ ጎረቤቶቿም አለኝታ አለመሆኗን አመላክተው የሰላ ትችት ሰንዝረዋል። 

 የደን ቃጠሎ ተቋቋሚዎች ለአየር ንብረት እርምጃ ፕሬዚደንት ጆ ዶድስ በበኩላቸው የአውስትራሊያ አሁንም የደንጊያ ከሰልን ሙጥኝ ባይነት አሳፋሪ ነው ሲሉ ሄሰዋል። 

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ድርጅት በፊናው የባሕር ከፍታ መጨመር ጥንታዊ ባሕሎች ቀዬዎቻቸውን ለቅቀው አገር የለሽ ስደተኞች እንዲሆኑ ያደርጋል በማለት ስጋቱን ገልጧል።

በዓለም አቀፍ መድረክ የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ስምምነቱ ስጥቶ መቀበል ላይ የተመሰረተ መሆኑን በበጎነት አንስተው፤ ሆኖም በቂ አለመሆኑን አመላክተዋል።

ግሪንፒስ በበኩሉ አደንጊያ ከሰል ዘመን እያበቃ ነው ብሏል። 

 

የወንጀል ተጠያቂነት ዕድሜ

 

 የቪክቶሪያ ነባር ዜጎች የሕግ አገልግሎት። አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በወንጀል ተጠያቂነት ዕድሜ ወደ 14 ከፍ እንዲል ጠየቁ።                                                 

የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪዎቹ የማሻሻያ እቅዳቸውን ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቅዳሜ ኖቬምበር 13 አቅርበዋል። 

በማሳመኛ አቅርቦታቸው ላይም የሕክምና ማስረጃና ዓለም አቀፍ ደረጃዎች በአንስተኛ አንድ ልጅ በወንጀል ሊጠየቅ ያስችለዋል የሚለው ዕሳቤ 14 ዓመት እንደሁ ጠቅሰዋል።


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now