- የትምህርት ቤቶች መከፈት እየተቃረበ እንደመምጣቱ መጠን ፤ እድሜያቸው ከ 5- 11 የሆኑ ሕጻናት ከአሁን ጀምሮ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ይችላሉ።
 - ሌተናንት ጀነራል ጆን ፍሪወን እንዳሉት ከሉት 10,000 የክትባት መስጫዎች ውስጥ አብዛኞቹ ለህጻናቱ ክትባቱን መስጠት የሚችሉ ናቸው ፤ ወላጆች ይህንን በመገንዘብ ቀጠሮዎች በሙሉ ላይገኙ ይችላሉ ብሎ ከመገመት በተደጋጋሚ መሞከር ይኖርባቸዋል።
 - ስኮት ሞሪሰን አዲስ መመሪያ ይፋ መሆኑን ያሳወቁ ሲሆን ፤ በተለይም አስፈላጊ በሚባሉ የሰራ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎች የቅርብ ንክኪ ቢኖራቸውም ፤ ሙሉ ለሙሉ ከተከተቡ እና የኮቪድ-19 ምልክቶችን እስካላሳዩ ድረስ ራሳቸውን ለይቶ ማቆየት አይጠበቅባቸውም ።
 - በኩዊንስላድ ተማሪዎች በፌብሩዋሪ 7 ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደሚመለሱ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ቀድሞ ታቅዶ ከነበረው ጃንዋሪ 24 በሁለላት ሳምንት ዘግይቶ ነው ።
 - በኒው ሳውዝ ዌልስ 2,030 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ፤ ከነዚህም መካከል እሁድ ይፋ ከሆነው ቁጥር 1,927 የሚሆኑት ውስጥ159 ያህሉ ከፍተኛ እንክብካቤ በሚያስፈልገበት ክፍል የሚገኙ ሲሆን ተጨማሪ 151 በዚሁ ይገኛሉ ።
 - በቪክቶሪያ በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሆስፒታል የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ከ752 ወደ 818 ከፍ ብሎ አድሯል ።
 - በኩዊንስላድ 419 ሰዎች በሆስፒታል ክትትል የተደረገላቸው ሲሆን ከነዚህ መካከልም 21 የሚሆኑት ከፍተኛ እንክብካቤ በሚያስፈልገበት ክፍል የሚገኙ ሲሆን የተቀሩት 7ቱ የመተንፋሻ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ።
 - በቪክቶሪያ ሶስተኛው የኮቪድ-19 ክትባት በተወሰኑ የስራ መስኮች ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች ግዴታ እንደሚሆን የጤና ሚኒስትሩ ማርቲን ፎሌይ አስታውቀዋል ።
 - የኒው ሳውዝ ዌልስ ፕሪምየር ዶሚኒክ ፔሮቴት ተጨማሪ 50 ሚሊየን ፈጣን የመመርመሪያ ቁሳቁሶችን ማዘዛቸውን ያሳወቁ ሲሆን ፤ ይህም የክለሉን አጠቃላይ ቁጥር ወደ 100 ሚሊዮን ከፍ ያደርገዋል ።
 - የኒው ሳውዝ ዌልስ መንግስት በፈጣን መመርመሪያዎች የሚገኙ ወጤቶች ከያዝነው ሳምንት ጀምሮ ኒው ሳውዝ ዌልስ ሰርቪስ አፕ እንደሚመዘገብ ይፋ አድርጓል
 
- አብዛኛዎቹ ክልሎችም በፈጣን መመርመሪያ የሚገኙ ውጤቶችን የሚመዘግቡበት ቅጾችን አዘጋጅተዋል ።
 
የኮቪድ -19 አሀዛዊ መረጃዎች
ኒው ሳውዝ ዌልስ  በፒ ሲ አር በተመረመረ ምርመራ 20,239 በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀ ሲሆን 18 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል ። ኒው ሳውዝ ዌልስ በፈጣን መመርመሪያ የሚገኙ ውጤቶችን ገና መመዝገብ አልጀመረችም ።
ቪክቶሪያ 34,808 ዜጎቿ በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ሁለት ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል ።
ኩዊንስላድ ቢያንስ 9,581 ሰዎች መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን ባለስልጣናቱ የተቀሩትን በ ፒ ሲ አር እና በፈጣን መመርመሪያዎች የተወሰዱትን ወጤቶች በመቁጠር ላይ ናቸው ።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 939 አዲስ ተያዦችን ያስመዘገበ ሲሆን በታዝማንያም 1,218 ሰዎች ተይዘዋል ።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ 
የገንዘብ እርዳታ 
 የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ከ 70 እና 80 በላይ ከሆነ ጀምሮ የክፍለ ሀገሮች የኮቪድ-19 የአደጋ ጊዜ ክፍያ ህጎች ተለውጠዋል 
- ዜናዎችን እና መረጃዎችን ከ 60 በላይ ቋንቋዎች ከ sbs.com.au/coronavirus
 - የየክፍላተ ሀገራቱን መረጃ በተመለከተ ፦ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania.
 - የኮቪድ-19 ክትባትን በቋንቁዎ መረጃን በተመለከተ ፦   COVID-19 vaccine in your language
- Visit the translated resources published by NSW Multicultural Health Communication Service
 
 - COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool. - የክፍላተ ሀገራቱን የመመርመሪያ ክሊኒኮች
 - NSW
 - Victoria 
Queensland
South Australia
ACT
Western Australia
Tasmania
Northern Territory 
·        
iframe src="https://www.sbs.com.au/labsembeds/vaccinated-dashboard-naca/index.html" data-module="iframe-resize_module"]
Share

