SKIP TO MAIN CONTENT

" ቁጥራቸው 27 የሆኑ ተለማማጅ ሐኪሞችና 2 ከፍተኛ ሐኪሞች በኮቪድ - 19 ተይዘውብናል" - ዶ/ር አሥራት አጸደወይን

*** ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

COVID - 19 Ethiopia
Asrat Atsedewoin (PhD), President of the University of Gondar Source: Supplied

1 min read

Published


Skip to article content

ለጎንደር ከተማና አጎራባች አካባቢዎች ህክምና በመስጠት በሚታወቀው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታልና ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚሰሩ ሁለት ከፍተኛ ሐኪሞችና 27 ተለማማጅ ሐኪሞች (Interns) በኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር አሥራት አጸደወይን ለSBS አውስትራሊያ ገልፀዋል።

ይህንን ተከትሎም ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ ለእነዚህ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እያደረገላቸው ነው ብለዋል።

"ተጋላጭ የሆኑበት ምክንያት ምንድን ነው?" በሚል ላቀረብናላቸው ጥያቄ ሲመልሱ  " በኮቪድ 19 ከተያዙት መካከል አዲስ አበባ ደርሰው የተመለሱ በመኖራቸው መነሻው ይህ ሊሆን ይችላል" የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልፀው "ይሁንና ዋናው ምክንያት እያጣራን ነው" ብለዋል።

ዶ/ር አሥራት ጨምረው እንደተናገሩት "የሕክምና ሥራ በባህሪው አጋላጭ እንደመሆኑ ሆስፒታሉ በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት የተጋላጭነት መከላከያ ቁሳቁሶችን ሲያቀርብ ነበር ፤ አሁንም እያቀረበ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

"የሆስፒታሉና የጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጁ ማኅበረሰብ በተፈጠረው አጋጣሚ ሳይደናገጥ ሕብረተሰቡን ማገልገሉን እንደቀጠለ ነው፤ ስርጭቱን ለመቀነስም እየሰራን ነው" ብለዋል ዶ/ር አሥራት።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now