- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 67 ፐርሰንት ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከተቡ
- የቪክቶሪያ ኮቪድ-19 ተጋላጨነት ሥፍራዎች ከ 1,000 ደረሱ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የኮሮናቫይረስ ገደብ እስከ ሴፕቴምበር 17 ተራዘመ
- ደቡብ አውስትራሊያ በኖርዘርን ቴሪቶሪ እና ኩዊንስላንድ ላይ ጥላ የነበረውን ገደብ አነሳች
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,164 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 796ቱ የምዕራባዊና ደቡባዊ ሲድኒ ነዋሪዎች ናቸው። ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ዋና የጤና መኮንን ዶ/ር ኬሪ ቻንት የጊልፎርድ፣ ሜሪላንድስ፣ ኦበርን፣ ግሪነኤከር፣ ባንክስታውንና ብላክታውን ነዋሪዎች እንዲመረመሩ አሳሰቡ።
የጤና ሚኒስትር ብራድ ሃዛርድ በቂ የፋይዘር ክትባት ስለሌለ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ አስትራዜኔካ ክትባትን እንዲከተቡ ምክረ ሃሳብ ቸሩ።
ሰኞ ዕለት የደቡብ ምዕራብ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪ የሆነ የመጀመሪያው አንድ የነባር ዜጎች ሰው ሕይወት በኮቪድ-19 ማለፉ ተነግሯል።
የኮቪድ-19 ክትባት ቀጠሮዎን ዛሬውኑ ያስይዙ book your COVID-19 vaccine
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 76 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 31ዱ ቫይረሱ ከተስፋፋባቸው ሥፍራዎች አይደሉም።
እንደራሴ አንድሩስ በነገው ዕለት የሚረግቡ ገደቦችን ለማስታወቅ ዕቅድ ይዘዋል። "ትክክለኛው ክትባት ሊከተቡት የሚችሉት ክትባት ነው" በማለትም በርካታ የአስትራዜኔካ ክትባት መኖሩንና ሰዎችም እንዲከተቡት አበረታተዋል።
ሜልበርን ውስጥ በርካታ የአፓርትመንት ሕንጻዎችን አካትቶ ከ 1,000 በላይ የተጋላጭነት ሥፍራዎች አሉ list of exposure sites
በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 13 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ስምንቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
የካንብራ አዲሱ የኮቪድ-19 መጠነ ሰፊ የክትባት ክሊኒክ የአውስትራሊያ ስፖርት ኢንስቲትዩት ውስጥ ሴፕቴምበር 3 ይከፈታል። ከሐሙስ ሴፕቴምበር 2 ከቀትር በኋላ 5pm ጀምሮ እስከ ሴፕቴምበር 17 ድረስ የሚቆዩ አዲስ ገደቦች ተጥለዋል new restrictions in place from 5pm on Thursday.
የኮቪድ-19 ክትባት መመዘኛን የሚያሟሉ መሆንዎን ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccination.
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ደቡብ አውስትራሊያ ከደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ እና ከካትሪን ኖርዘርን ቴሪቶሪ ተጉዘው ለሚመጡ ጥላቸው የነበሩትን ገደቦች ሁሉ አነሳች
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

