የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ከ600 ያህል ቀናት በኋላ ዓለም አቀፍ ድንበሮች ለአውስትራሊያውያን ተከፈቱ

*** ሙሉ ክትባት የተከተቡ በኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያና የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የሚገኙ የአውስትራሊያ ዜጎችና ቋሚ ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ልዩ ፈቃድ ሳይጠይቁ ከአገር መውጣትና ወደ አገር ሲመለሱም ወሸባ መግባት ግድ አይሰኙም።

COVID-19 update

Travellers arriving on the first quarantine free international flights are embraced by family at Sydney International Airport, Monday,November 1, 2021. Source: AAP

ጉዞ

  • ሙሉ ክትባት የተከተቡ በኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያና የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የሚገኙ የአውስትራሊያ ዜጎችና ቋሚ ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ልዩ ፈቃድ ሳይጠይቁ ከአገር መውጣትና ወደ አገር ሲመለሱም ወሸባ መግባት ግድ አይሰኙም።

  • የአውስትራሊያ ዜጎችና ቋሚ ነዋሪ ወላጆችም ከዛሬ ጀምሮ ወደ አውስትራሊያ በ Travel Exemption Portal በኩል አመልክተው መምጣት ይችላሉ።

  • ሙሉ ክትባት የተከተቡ የሲድኒና የሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሲድኒና ወደ ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ መጓዝ ይችላሉ። 

  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ የመግቢያ ፈቃድ በወሰን አካባቢ ባሉ ነዋሪዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚነት አይኖረውም። 

  • ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ሙሉ ክትባት ያልተከተቡ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ወደ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ለሽርሽር መሔድ አይችሉም።

  • ሙሉ ክትባት የተከተቡ ካንብራውያውያን ወደ ኒው ሳውዝ ዌይልስና ቪክቶሪያ መጓዝ ይችላሉ። 

የክትባት አሰጣጥ

  • የኮቪድ-19 ሁለተኛ ዙር ክትባት ከተከተቡ ስድስት ወር ያለፋቸው የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጎልማሶች የሶስተኛ ዙር ማጠናከሪያ ክትባት በአካባቢያቸው ከሚገኙ መድኃኒት ቤቶች፣ ወይም ጠቅላላ ሐኪማቸው ዘንድ አለያም ወደ ክትባት ማዕከላት በመሔድ መከተብ ይችላሉ።

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ

  • ቪክቶሪያ ውስጥ 1,471 በኮሮናቫይረስ ሲጠቁ አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 135 በቫይረስ ሲጠቁ አራት ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።
 


Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service